በተለምዶ ጥቅምት ወር ብረድ እንጂ እምብዛም ዝናብ አይታይበትም። ይኸውና ክቡር አባታችን ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ሙፍቲ በስጋ ተለይተውን ቅድስት ነፍሳቸውን ወደ ጀነት፣ ክቡር ሰጋቸውን ደሞ ወደ ምድር በሚመለስበት ቀን “ ሰማዩም አለቀሰላቸው።” ( ሰማዩ ዝናቡን ለቀቀው )።
እኔ በሄድኩበት ወይም ክቡር አስከሬናቸው ለመሸኛ በተዘጋጀበት “ ቦሌ ሚለንየም አዳራሽ “ አካባቢ ሙቀት የቀላቀለበት ከበድ ያለ ዝናብ ነው የዘነበው።
ዝናብ ዘነበ ሳይሆን፣ ለክቡር አባታችን
“ ሰማዩም አለቀሰላቸው “ ብዬ ነው የወሰድኩት።
እወነት ለመናገር እኔ ካለሁበት እምነት አንድ ትልቅ ሊቀጳጳስ በህይወት የተለየ ያህል እየተሰማኝ….
….“ ብፁዕ አባታችን “ የሚለው ቃል አስሬ አፌ ላይ ይመጣብኛል። ይህንን ፅሁፍ እንኳን ሰፅፍ አፌላይ የሚመጣብኝ “ ብፁዕ አባታችን “ የሚለው ቃል ነው።
ለሙስሊም ወገኖቼ
ብፁዕ አባታችን ማለት ጳጳስ፣ ሊቀጳጳስ ማለት ሲሆን። በሀይማኖታችን ትለቅ ማዕረግ የደረሱ የሀይማኖት አባቶቻችን ማለት ነው።
ክቡር አባታችን እንኳን ንግግር አድርገው አደለም፣ ለጉባኤ እንኳን አዳራሽ ውስጥ ሲታደሙ የአዳራሹ ግርማ ሞገስ ጎልቶ ይታያል።
እርስዎን በማጣታችን እጅጉን ብዙ ነገር ነው የጎደለብን።
ክቡር አባታችን እኛ ልጆችዎ እንወድዎታለን እናከብሮታለን።
ሀገራችን ኢትዮጵያም ታመሰግኖታለች።
ቅድስት ነፍስዎን በአባቶቻችን እቅፍ ያኑርልን።
አሜን
እማከብርዎ እምወድዎ የመንፈስ ልጅዎ
ሰሎሞን አማረ።