ከተጀመረ ዓመታትን ያስቆጠረው የዩኒቨርሰቲ ኢንዱስትሪ ትስስር

Date:

ለተግባር ልምምድ የተላኩላቸውን ተማሪዎች ተገኝተዋል ለማለት ብቻ ፊርማ እያስፈረሙ የሚሸኙ ኢንዱስትሪዎች አሉ ተብሏል።

ሌሎቹ ደግሞ ውድ የሆኑ ማሽኖቻችንን ያበላሹብናል በሚል ተማሪዎቹ ወደ ስራው እንዳይቀርቡ ያከላክላሉ ተብለው ተወቅሰዋል ።

ከዚህ በኋላ ግን አሰራሩ ላይ መሰረታዊ ለውጥ እንደሚደረግ ሠምተናል።

ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን ለተግባር ልምምድ ወደ ኢንዱስትሪዎች የሚልኩበት መርሃ ግብር አሁንም የተለያዩ ችግሮች ያሉበት እንደሆነ ተነግሯል።

ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ለተግባር ልምምድ ወደ ተቋማቱ ሲልኩ መርሃ ግብሩን ለማሟላት እንጂ ማግኘት ስላለባቸው ክህሎት በቂ ዝግጅት አያደርጉም ተብለው ይወቀሳሉ።

ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ለተግባር ልምምድ የሚኩላቸውን ተማሪዎች መከታተልና በአግባቡ ማሰራት ላይ ክፍተት እንዳለባቸው ይነሳል።

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ስር የሚገኘውን የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትር ትስስር የሚመራው ቡድን አስተባባሪ የሆኑት ኢንጂነር ጌትነት በላይም ይህንኑ ሃሳብ ያጠናክራሉ።

አብዛኞቹ ኢንዱስትሪዎች በደብዳቤ የተመደቡላቸውን ተማሪዎች ተቀብለው በየቀኑ እያስፈረሙ ከመሸኘት ያለፈ ስራ እየሰሩ አይደለም ብለዋል።

ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ ግን አሰራሩ እንደሚቀየር ኢንጂነር ጌትነት ነግረውናል።

አንዱ ለውጥ በአብዛኛው በዩኒቨርሲቲዎች ይደረግ የነበረውን የተማሪዎቹን የብቃት ምዘና በኢንዱስትሪዎች እንዲካሄድ ማድረግ ነው ብለዋል።

ከሰባ በመቶ በላዩ የተማሪዎች ምዘና በኢንዱስትሪዎች እንደሚሆን ጠቅስዋል።
ኢንዱስትሪዎች ለተግባር ልምምድ የተላኩላቸው ተማሪዎች ማሽኖችን ያበላሻሉ ወይም ይሰብራሉ በሚል ስጋትም ወደ ስራው እንዳይቀርቡ እንደሚያከላክሉ ተነግሯል።

ውድ የሆኑትን ማሽኖች መተካት የራሳቸው ሃላፊነት ስለነበር ወደ ማከላከሉ እንደገቡ የሚናገሩት ኢንጂነር ጌትነት ከዚህ በኋላ ግን ይህም የእነሱ ብቻ ራስ ምታት አይሆንም ብለዋል።

ከዩኒቨርሲቲዎች በተጨማሪ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትም ተማሪዎቻቸውን ወደ ኢንዱስትሪዎች ልከው የተግባር ልምምድ እንዲወስዱ እንዲወስዱ እንዲያደርጉ የማስተሳሰር ስራ ይሰራል ተብሏል።

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል፡፡ በሥርዓተ...

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስክሬን ሽኝት በሚሊንዬም አዳራሽ ተካሂዷል

የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ታየ አጽቀስላሴ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት...

ሸህ ዑመር ገነቴ!!!

እንዲህ ወደ ደገር…እንዲህ ወደ ገታ…ደግሞም ወደ ዳና፤ጫሌ ገንደጎራ፤የተሰየማችሁ፤ሰው መሆን…..ሰው...