ከ290 በላይ ሐኪሞች በአጥንት ቀዶ ሕክምና ስፔሻላይዝድ በማድረግ ላይ ናቸው

Date:

የአጥንት ቀዶ ሕክምና አገልግሎት አሰጣጥን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማጎልበት ከ290 በላይ ሐኪሞች በስፔሻላይዜሽን ትምህርት ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ የአጥንትና የአደጋ ሕክምና ስፔሻሊስቶች ብሔራዊ ማኅበር አስታውቋል።

ማኅበሩ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ዜጎች በተፈጥሮ እና በሰው ሠራሽ አደጋዎች ምክንያት ለሚገጥማቸው የአጥንት ስብራትና አካላዊ ጉዳት በብቁ ባለሙያዎች ቀዶ ሕክምና እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ነው።

የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ኤፍሬም ገብረሃና (ዶ/ር) እንዳሉት፣ በሀገር ውስጥ እየተሰጠ ካለው የስፔሻላይዜሽን ትምህርት በተጨማሪ፤ 10 ሐኪሞች ወደ ተለያዩ የውጭ ሀገራት ተልከው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

የአጥንት ቀዶ ሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ከሕዝብ ቁጥሩ አንጻር እጅግ አናሳ መሆኑን የገለጹት ፕሬዘዳንቱ፤ በበቂ ሁኔታ ተደራሽ ለማድረግ ማዕከላትን በማስፋት ዘመናዊ የአጥንት ቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት በመሰራት ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

ማኅበሩ በዚህ ዓመት ለ18ኛ ጊዜ “በመረጃ የተደገፈ ዘመናዊ የአጥንት ሕክምና በማድረስ ክፍተትን መሙላት” በሚል መሪ ቃል ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

አጠቃላይ በዚህ ጉባኤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰሩ ከ500 ያላነሱ ባለሙያዎች እና በዘርፉ የላቀ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የክብር እንግዶች በተገኙበት የፓናል ውይይት እየተደረገ ነው።

የኢትዮጵያ የአጥንትና የአደጋ ሕክምና ስፔሻሊስቶች ብሔራዊ ማኅበር በሀገር አቀፍ ደረጃ የአጥንት፣ መገጣጠሚያና የጡንቻ ሕክምናን ለማዘመን፣ በስፋትና በጥራት ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ የሚገኝ ሀገር አቀፍ ማህበር ነው።

በግንቦት 1995 ዓ.ም የተመሠረተው ማኅበሩ በ13 ተቋማት ላይ የአጥንት ቀዶ ሕክምና ለሚሰጡ ሐኪሞች ስልጠና እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፤ እስከ አሁን ወደ 700 የሚጠጉ አባላት እንዳሉት ተመላክቷል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

BYD ከ115,000 በላይ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ ማሻሻያ እንደሚያስፈልጋቸው ገለጸ

የቻይናው ግዙፉ የኤሌትሪክ መኪኖች አምራች ቢ.ዋይ.ዲ በዲዛይንና በባትሪ ተከላ...

የትራምፕን ንግግር የህንድ መንግስት ስለ ጉዳዩ ምንም የማዉቀዉ ነገር የለም ብሏል

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሩሲያን ነዳጅ ላለመግዛት መስማማታቸውን...

አቶ አህመድ ሽዴ ከእንግሊዝ የዓለም አቀፉ የልማት እና የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከእንግሊዝ የአለም አቀፍ የልማት...