ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ዜሌንስኪ ጀግና ነው” ሲሉ የተናገሩት ከእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኬር ስታመር ጋር በሩሲያ ዩክሬይን የሠላም ድርድር ሂደት ላይ በነጩ ቤተመንግሥት ተገናኝተው ከመከሩ በኋላ ነው።
በዛሬው ዕለት ከዩክሬይኑ ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ ጋር ተገናኝተው እንደሚመክሩ የሚጠበቁት ትራምፕ “ዜሌንስኪ አምባገነን እንደሆኑ ያስባሉ ወይ” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ” ብዬ ነበር እንዴ? ይህንን ማለቴን ማመን አልችልም” ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።
የሠላም ውይይቱን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄም “በሚፈለገው ፍጥነት እየሄደ ነው” ብለውታል።
ዜሌንስኪ እና ትራምፕ ሲገናኙም የማዕድን ሥምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።