የመጀመሪያውን ትራንስፎርሜሽናል ባንክ ዕውቅና ማግኘቱ ታወቀ

Date:

በስርዓተ ፆታ አካታችነት ምዘና መስፈርት “የኢትዮጵያ ባንኮች የመጀመሪያው ትራንስፎርሜሽናል ባንክ “መባሉን እናት ባንክ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዓለም ባንክ የሥርዓተ-ፆታ ፈጠራ ጋር በመተባበር ባካሄዱት የ2025 የባንኮች የስርዓተ ፆታ አካታችነት ምዘና መስፈርት መሰረት ነው እናት ባንክ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ባንኮች የመጀመሪያ በመሆን ትራንስፎርሚሽናል ባንክ መባሉን የገለጸው።

የእናት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን ይህን ያሉት በዛሬው ዕለት ባንኩ በአዲስ አበባ ፒያሳ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት አካባቢ በቀድሞው የማስታወቂያ ሚኒስቴር ህንጻ “እማዬ” የተሰኘውን ቅርንጫፍ ባስመረቀበት ወቅት ነው።

ወ/ሮ አስቴር ፤ እናት ባንክ በፒያሳ  ቅርንጫፉ የሴቶች አካታችነትን በማስፋት ሴቶች በአገራችን  ኢኮኖሚ  ተጠቃሚ  እንዲሆኑ ትልቅ  እድል ይፈጥራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እናት ባንክ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበት ሁሉን አቀፍ የሴቶች አካታች የባንክ አሰራርን አጠናክሮ  እንደሚቀጥል  የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን ገልፀዋል።

በቀጣይ እናት ባንክ በመላ አገሪቱ  የቅርንጫፍና የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት  ተደራሽነቱን በማስፋት አዳዲስ አካታች የባንክ አሰራሮችን በመተግበር  በአካታች የባንክ አሰራር የተገኙ  ውጤቶችን ይበልጥ አጠናክሮ  እንደሚቀጥል  ተናግረዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የህዳሴ ግድቡ ውዝግብ በፖለቲካዊ ሳይሆን በቴክኒካዊ መንገድ መፈታት አለበት

በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ፣ እና የመካከለኛው ምስራቅ...

የ7 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ አለመከናወኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሚተዳደሩ 7 የጋራ መኖሪያ...

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ በ80 ዓመታቸው ከዚህ...