ጆን ቦልተን በሪፐብሊካኑ የመጀመሪያው ዙር የፕሬዚዳንትነት ወቅት የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ነበሩ።
በአሁኑ ሰዓት በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ብርቱ ትችት በመሰንዘርም ይታወቃሉ።
የአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ክሱን በሜሪላንድ ለዳኞች አቅርቧል።
ይህንም ተከትሎ ዳኞቹ (ግራንድ ጁሪ የ23 ባለሙያዎች ስብስብ) ጆን ቦልተን ክስ እንዲመሰረትባቸው ተስማምተዋል አሊያም በቂ ምክንያት አለ ብለዋል።
ጆን ቦልተን ምስጢራዊ መረጃዎችን የያዙበትን መንገድ በመተቸት የፌደራል ምርመራ ቢሮው ነሐሴ ላይ ቤታቸውን እና ቢሯቸውን መፈተሹ የሚዘነጋ አይደለም።
የሰባ ስድስት ዓመቱን ጆን ቦልተን ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በትራምፕ ፖለቲካ ላይ ጥያቄ በማንሳት ከተወነጀሉ ሶስት ሰዎች መካከል አንደኛው ያደርጋቸዋል።
የኒውዮርክ ጠቅላይ አቃቤ ህግ እና የኤፍ ቢ አይ ዳይሬክተር የቦልተን ዕጣ ፈንታ የደረሳቸው ናቸው።
በምስጢራዊ ሰነድ አሳልፎ መስጠትና አያያዝ እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች በጥቅሉ 18 ክሶች ቀርበውባቸዋል።
የግላቸውን ኢ-ሜይል እና ሌሎች የመልዕክት ማስተላለፊያዎችን በመጠቀም ስለአሜሪካ መከላከያ መረጃ አጋርተዋል ተብሏል።
ሰነዱ ወደ ፊት ስለሚደረጉ ጥቃቶች፣የውጭ ጠላቶና የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን ያካተተ በመሆኑ በቀላሉ የሚታይም አይደለም ።
ጥፋተኝነታቸው ከተረጋገጠ ደግሞ እስከ አስር ዓመትም ዕስር ይጠብቃቸዋል።
ጆን ቦልተን በ2019 ከመጀመሪያው የትራምፕ አስተዳደር መባረራቸውም የሚታወስ ነው።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
NBC Ethiopia