ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከአይ ኤም ኤፍ እና የዓለም ባንክ አመታዊ ስብሰባዎች ጎን ለጎን በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የአፍሪካ ግሩፕ ሶስት ቀጣይነት ስምምነት ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል።
ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በአይ ኤም ኤፍ ኮታ ላይ የተደረገው የሃምሳ በመቶ ጭማሪ ለአለም አቀፍ ፋይናንሺያል ሴፍቲኔት መጠናከር እና ለአባል ሀገራት የሃብት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚረዳ አዎንታዊ እርምጃ መሆኑን በመገንዘብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተወሰደውን አርምጃ እንደሚቀበል ገልፀዋል።
ይህ እርምጃ በአሁን ወቅት ያለውን የአለም ኢኮኖሚ ገጽታ በተሻለ መልኩ ከሚያንፀባርቅ ወቅታዊ እና ፍትሃዊ የኮታ ማስተካከያ ጋር ማጣጣም አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።
ዶ/ር ኢዮብ የኮታ ጭማሪው እና ፈጣን አተገባበሩ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ገልፀው፣ የኮታ ማስተካከያ አጣዳፊነት ግን እጅግ ከፍ ያለ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አስረድተዋል።
የታዳጊ አባል ሀገራት የኮታ ድርሻን መጠበቅ ላይ እየታየ ያለውን ስምምነት በማድነቅ፣ አሁን ባለው ማዕቀፍ ውስጥ ታዳጊ ሀገራት ያላቸውን ዝቅተኛ ውክልና መፍታት አስፈላጊ መሆኑን ዶ/ር ኢዮብ አጽንዖት ሰጥተዋል።
ፍትሃዊ፣ ሚዛናዊ እና ሁሉን አቀፍ የሆነ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓትን ለማረጋገጥ ወደፊት በሚደረጉ የኮታ ማስተካከያዎች እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ዝቅጠኛ ውክልና ያላቸው ሀገራት ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል።
AMN