የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል፡፡ በሥርዓተ ቀብሩ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ኡለማዎች፣ ደረሳዎች፣ ኡስታዞች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል።
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ከ2010 መጋቢት እስከ ግንቦት ወር 2014 ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በፕሬዚዳንትነት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ በመሆን አገልግለዋል፡፡
