የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስክሬን ሽኝት በሚሊንዬም አዳራሽ ተካሂዷል

Date:

የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ታየ አጽቀስላሴ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ፣ የጠቅላይ ምክርቤቱ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ፣የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች ፣የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ ዑለማዎች ፣ ዱዐቶች የተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ ወዳጆች እና ቤተሰቦች በተገኙበት ነው ሽኝቱ የተካሄደው።

በስነስርዓቱ መልክእት ያስተላለፉት ፕሬዝደንት ታየ አጽቀስላሴ “ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው አጥታለች” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ “ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር የሁላችንም አባት የሰላም ምልክት ነበሩ፣ በእጅጉ አዝነናል” ብለዋል።

በስነስርዓቱ የክብር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር በሀይማኖት አስተምህሮ እና ሁሉንም በሚያግባባ የሰላም ጥሪና ጥረታቸው በእጅጉ ታሪክ የሚዘክራቸው መሆኑ ተነስቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል፡፡ በሥርዓተ...

ሸህ ዑመር ገነቴ!!!

እንዲህ ወደ ደገር…እንዲህ ወደ ገታ…ደግሞም ወደ ዳና፤ጫሌ ገንደጎራ፤የተሰየማችሁ፤ሰው መሆን…..ሰው...

እንኳን ሰው ሰማዩም አለቀሰላቸው

በተለምዶ ጥቅምት ወር ብረድ እንጂ እምብዛም ዝናብ አይታይበትም። ይኸውና...