የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአለም ላይ ያሉ የስደተኞች ቁጥር የሚያሳየዉ “ሁከት የዘመናችን መገበያያ ገንዘብ መሆኑን ነዉ” ብሏል

Date:

የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በአለም ላይ እየጨመረ በመጣዉ በስደተኞች ቁጥር በኩል ወቅታዊ መረጃን በዛሬዉ እለት በሰጠበት ወቅት ነዉ ይህንን ያለዉ፡፡

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ለፀጥታው ምክር ቤት ሁኔታዉን ሲገልጹ፤”ሁከት የዘመናችን ዋነኛ መገበያያ ገንዘብ ሆኗል” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ግራንዲ በአለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ተባብሶ በቀጠለው በየሃገሪቱ ባለዉ ግጭቶች ምክንያት ዜጎች ክፉኛ ችግር ዉስጥ ይገኛሉም ብለዋል።

በተለይ ወደ ሰባት ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኞች ከሱዳንና ዩክሬን የተፈናቀሉ መሆናቸዉንም ኮሚሺነሩ ጠቁመዋል፡፡

ኮሚሺነሩ አክለዉም”በአጭርና በረጅም ጊዜ ደህንነታቸው የተጠበቀና አስተማማኝ ዋስትና እስካልተሰጣቸዉ ድርስ ተፈናቃዮችን ወደ ስፍራቸዉ መመለስ አይቻልም” ብለዋል ሲል የዘገበው የአፍሪካ ኒዉስ ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብሮች

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ። ዛሬ ሰባት...

ለዩክሬን ሰላም ‘በጣም ተቃርበናል’ ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬኑ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በትናንትናው...

በዲማ የአለባበስ ቅጣት

በጋምቤላ ክልል ዲማ ከተማ ከባህል ውጪ በሆነ አለባበስ ምሽት...