በመቐለና ዙሪያዋ የሚገኙ የትግራይ ኃይል አባላይ ትናንት ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 እስከ ምሽት ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደው ነበር።
በዚያው ቀን ምሸት የሰላማዊ ሰልፈኞቹ ተወካዮች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ከሚገኙባቸው የህወሓትና የሰራዊት አዛዦች ቢነጋገሩም ፤ ስለተደረሰው ስምምነት በይፋ ለህዝብ የተሰጠ መረጃ የለም።
ሆኖም ከሰብሰባው አዳራሽ ተቆርጦ የወጣው ቪድዮ እንደሚያመለክተው ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የደመወዝ ፣ የጥቅማጥቅምና ለቤተሰቦቻቸው መኖሪያ የሚውል የመስሪያ ቦታ ጥያቄ አንስተዋል።
የትናንትናው ውይይት ውጤት ለህዝብ ሳይነገር ታድያ ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ወደ መቐለ ከተማ የሚያስገባው ዋና አስፋልት ከጥዋት ጀምሮ ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰዓትና ደቂቃ በሁለት ቦታ ተዘግተዋል።
የትግራይ ኃይል አባላት ሰላማዊ ሰልፈኞች ኣጉላዕና ጉርመዶ በሚባሉ ሁለት ቦታዎች መንገድ በመዝጋታቸው ምክንያት መኪኖች ቆመዋል ተጓዦች ተስተጓጉለዋል።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸው ከትናንትናው ሰልፍ ተመሳሳይ እንደሆነ ቦታው ድረስ ተደውሎ ተረጋግጧል ።
@tikvahethiopia