የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ቤት ወይም ቪላ አልፋ እድሳት ተጠናቀቀ

Date:


የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ቤት ወይም ቪላ አልፋ እስከ ጥቅምት 2018 ለሕዝብ ክፍት ይሆናል ቢባልም፤ ክፍት ከመደረጉ በፊት መሰራት ያለባቸው ሥራዎች ገና ባለመጠናቀቃቸው እስከ ሚያዚያ ወር ሊቆይ እንደሚችል ነው የተገልጿል፡፡

የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ በሚያዚያ 2 ቀን 2004 ዓ.ም ካረፉ በኋላ ዝግ ሆኖ እስካሁን የዘለቀው ቪላ አልፋ፤ የተለያዩ የጥገና ሥራዎች እየተሰሩለት ነው ቢባልም ግን ለሕዝብ እይታ ተከልክሎ 14ኛ ዓመቱን ይዟል፡፡

ቪላ አልፋ የጥገና ሥራው ከመጀመሩ በፊት ውስጡ ያሉት ተንቀሳቃሽ የጥበብ ሥራዎች እና ሌሎችም ንብረቶች ወደ ቅርስ ባለ-ስልጣን መስሪያ ቤቱ እንዲሄዱ ተደርጎ እንደነበርም የሚታወስ ነው፡፡

ከመሬት በታች በሚወጣ እና ከላይ በሚዘንብ ዝናብ ቪላ አልፋ በጣም ተጎድቶ ነበር፤ አሁን ላይ ግን ከውጭ ሀገራትም ይሁን ከሀገር ውስጥ የአርቲስቱን ሥራዎች እየተመለከቱ ባለሙያዎች ትምህርት ለመውሰድ በሚችሉበት ደረጃ ጥገናው ተደርጓል ነው የተባለው፡፡

እንደ ሙዚየም የሚደራጅ በመሆኑ ጊዜ እንደወሰደም ነው የተገለጸው፡፡

የእድሳቱ ሥራ ተጠናቆ የርክክብ እና ቅርሶችን በቦታቸው የመመለስ ሥራዎች ብቻ ቀርቷል ሲሉም የብሄራዊ ሙዚየም መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዷለም ግርማይ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

“የእድሳቱ ሥራ ጥንቃቄዎችን የሚጠይቅ ነበር” ያሉት አቶ እንዷለም፤ የርክክብ ሥራዎች ሲጠናቀቁ ቪላ አልፋን በ2018 እስከ ሚያዚያ ወር ለእይታ ክፍት ለማድረግ ታስቧል ነው ያሉት፡፡

የእድሳት ሥራው 65 ሚሊየን ብር እንዳስወጣ ከዚህ በፊት የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የእድሳት ሥራው በምዕራፎች የተከፋፈለ ነበር ነው የተባለው፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢመማ 23ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ እና በአዳማ ከተሞች ተካሔደ

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 23ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻው ሥነ_ሥርዓት...

ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ...