የአምባሳደር መለስ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል

Date:

አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ”የኢትዮጵያ እናየ ኬንያ ስጋት እና ተስፋ” በሚል ርዕስ ያዘጋጁት አዲስ መጸሐፍ  በነሐሴ ወር መጨረሻ  ላይ ለንባብ እንደሚበቃ ተገለጸ፡፡

አገራቸውን በዲፕሎማሲው መስክ  ከሀያ ዓመታት  በላይ ያገለገሉት አምባሳደር መለስ ዓለም፤ በጋዜጠኝነት ሙያ መሥራታቸውም ይታወቃል፡፡

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ያገኙ ሲሆን፤ በትምህርቱ ዓለም የገፉበት መስክ ደግሞ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ ነው።

የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከናይሮቢ ዩኒቨርሲቲ፣ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ደግሞ ከስዊዘርላንድ የማኔጅመነት ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ግንኙነት አግኝተዋል።

አምባሳደሩ በኬንያ ማላዊና ሲሸልሰ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው አገራቸውን አገልግለዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል፣ በጎረቤት አገራት ዳይሬክተር ጄኔራልነትና በቃል አቀባይነት ያገለገሉም  ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው እየሠሩ ነው።

አምባሳደር መለስ ዓለም  ከአሁን በፊት በምሥራቅ አፍሪካ ላይ አተኩረው በሚሰሩ ጋዜጦች ላይ የአገራቸውን ጥቅም ያስቀደሙና ቀጣናዊ ትስስርን የሚያበረታቱ ጽሑፎችን አሳትመዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብሮች

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ። ዛሬ ሰባት...

ለዩክሬን ሰላም ‘በጣም ተቃርበናል’ ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬኑ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በትናንትናው...

በዲማ የአለባበስ ቅጣት

በጋምቤላ ክልል ዲማ ከተማ ከባህል ውጪ በሆነ አለባበስ ምሽት...