የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን (ኢማባ) ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አብዱልበር ሸምሱ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ሎጂስቲክስ (ኢባትሎ) ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ሆነዉ መሾማቸዉን የባለሥልጣኑ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
አብዱልበር ሸምሱ ከመጋቢት 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት መርተዋል።
በኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን በቆዩበት ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያን ሎጂስቲክስ ትራንስፎርም የማድረግ ሂደት እንዲፋጠን እና የሞጆ ደረቅ ወደብ የአረንጓዴ የሎጂስቲክስ ማዕከል መሰረተ ልማት ከነበረበት ችግሮች ተላቆ የመጨረሻ ምዕራፍ እንዲደርስ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ይነገራል።
CapitalNews