በሃማስና እስራኤል መካከል በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት የመጀመሪያው የታጋቾች የልውውጥ ሂደት መካሄድ ጀምሯል።
በዚህም ሀማስ ሰባት የእስራኤል ታጋቾችን ለቀይ መስቀል አስረክቧል። ቀይ መስቀልም የመጀመሪያ ታጋዮችን ለእስራኤል ወታደሮች ማስተላለፍ ተገልጿል ።
ታጋቾቹ በቀይ መስቀል እጅ መግባታቸውን የእስራኤል የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሲያስታውቁ፣ በሀገሪቱ በሚገኙ የህዝብ ማሳያዎች እና በቴል አቪቭ በሚካሄደው ዋና ዝግጅት ላይ የተሰበሰቡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን በታላቅ ደስታና ጩኸት ስሜታቸውን እየገለፁ ይገኛል ።
በተደረሰው ስምምነት መሠረት ሀማስ አጠቃላይ 20 በሕይወት ያሉ ታጋቾችን ለመልቀቅ ቃል ገብቷል:: በምላሹም እስራኤል በእስር ላይ የሚገኙ ከ1700 በላይ ፍልስጤማውያን እስረኞችን ትለቃለች ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ የመጀመሪያው የታጋቾች ልውውጥ ለሁለት ዓመት የዘለቀው አውዳሚ ጦርነትን ለማቆም በሚደረገው ጥረት ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ ተደርጎ ተቆጥሯል።