የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ የሊባኖሱን ሂዝቦላህ ቡድን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስጠንቅቀዋል፣ እስራኤልን በሚያስፈራሩ “አሸባሪዎች” ላይ ትዕግስትንችን ቀጭን ነው ሲሉ ዝተዋል።
“የሂዝቦላህ ዋና ፀሃፊ ከቀደምቶቹ ትምህርት እየተማረ አይደለም እናም በኢራን አምባገነን ትእዛዝ መሰረት በእስራኤል ላይ እርምጃ እንደሚወስድ እየዛተ ነው” ሲሉ ካትዝ በኤክስ ላይ በለጠፈው ጽሁፍ አጋርተዋል።
የሂዝቦላህ የቀድሞ መሪ ሀሰን ናስራላህ ባለፈው አመት እስራኤል በሂዝቦላ ላይ ባካሄደችው ዘመቻ መገደላቸው ይታወሳል።
“እስራኤላውያን በሚያስፈራሩ አሸባሪዎች ላይ ቴላቪቭ ትዕግስት እንዳጣች እንዲጠነቀቅ እና እንዲረዱት ለሊባኖሱ ሂዝቦላ ተግሳፅ አቀርባለሁ።
” የሂዝቦላህ መሪ ናኢም ቃሴም ሃሙስ ዕለት እንዳሉት የሊባኖስ ቡድን በኢራን ላይ እየተወሰደ ያለውን “ጨካኝ የእስራኤል-አሜሪካዊያን ጥቃት” ላይ እርምጃ ቡድኑ እንደሚወስድ አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል የሊባኖስ ተደማጭነት ያላቸው የፓርላማ አፈ-ጉባዔ ናቢህ በሪ፣ በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የሺዓ ፖለቲከኛ እና የሂዝቦላ የቅርብ አጋር ሲሆኑ ትናንት ምሽት ለሀገር ውስጥ ኤም ቲቪ ዜና ሲናገሩ ሊባኖስ በእስራኤል ግጭት ከኢራን ጋር እንደማትቀላቀል ያላቸውን ማረጋገጫ ገልፀዋል።
“ሊባኖስ ወደ ጦርነት እንደማትገባ 200 በመቶ እርግጠኛ ነኝ” ሲሉ ቤሪ ለዜና ምንጩ ተናግረዋል፣ ምክንያቱም ይህን ለማድረግ ምንም ፍላጎት ስለሌላት እና ብዙ ዋጋ ስለሚከፍል ነው ብለዋል።
አክለውም “ኢራን እኛን አትፈልግም። ድጋፍ የሚያስፈልገው ለእስራኤል ነው ሲሉ ተደምጠዋል።