“የከፊል ጊዜ ጸሐፊ ነኝ” የምትለው ሕይወት ተፈራ ከሀገር ከወጣች ከዘመናት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሳ ‘Tower In The Sky’ በሚል መጽሐፏ ከአንባቢ ጋር ተዋወቀች።
የኢሕአፓን ዘመን ከራሷ አንጻር የተረከችበት ይህ መጽሐፍ የእሷን አቻዎቿን የወጣትነት ዘመናት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ስለነበር ተወደደላት። ከዚያ በኋላም ሦስት ያህል መጻሕፍትን በእንግሊዘኛ እና በአማርኛ ማስነበብ ችላለች።
የሥነ ሰብ ጥናት (አንትሮፖሎጅ) የትምህርት መስኳ ሲሆን፣ በሐረር ተወልዳ፣ በአዲስ አበባ ተምራ ወደ ካናዳ አቅንታ ብዙ የሕይወት ልምድን ቀስማለች።
ሙዚቃ ማድመጥ እንደምትወድድ የምትናገረው ሕይወት ተፈራ፣ የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 25ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የምንጊዜም ሦስት ምርጥ ዘፈኖቿን አሳውቃለች።
እነዚህም፦
የጥላሁን ገሠሠ “በምሽት ጨረቃ”
የሚካያ በኃይሉ “ሀገሬ”
የቴዎድሮስ ካሣሁን “ማ ዘንድ ይደር” ናቸው።
#FM97_1