የድምፃዊ ይሁኔ በላይ የጥበብ እና የህይወት ጉዞውን የሚያስቃኝ አዲስ መጸሐፍ ለንባብ ሊበቃ እንደሆነ ተሰምቷል።
“ፍኖተ ጥበብ” የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መጽሐፉ ድምጻዊ ይሁኔ በላይ ከተወለደበት ፍኖተ ሰላም እስከ አሜሪካ በሙዚቃ ህይወቱ እና በኑሮ ያሳለፈውን የሕይወት ጉዞ የሚተረክበት ነው ተብሏል።
በመጽሐፉ ዝግጅት ላይ ደራሲ አቤል ጋሼ እና መጋቢ ጥበባት አበረ አዳሙ በአርትኦት ስራ ተሳትፉበታል።
መጽሐፉ በፈረንጆቹ ሰኔ 21 2025 በአሜሪካ ሀገር የሙያ ባልደረቦቹ በተገኙበት ይመረቃል ተብሏል።