የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል ፓርላማ ተገኝነተው እያካሄዱ የሚገኙትን ንግግር አንድ እስራኤላዊ የፓርላማ አባል አስተጓጉለዋል፡፡
የእስራኤል ፓርላማ አባል የሆኑት እኚህ ግለሰብ ለፍልስጤም እውቅና ይሰጥ የሚል ፅሁፍን በመያዝ እና በማስተጋባት የትራምፕን ንግግር አቋርጠዋል፡፡
ግለሰቡን የክነሴት አባላትና የደህንነት ባለሞያዎች በፍጥነት ከፓርላማው ለቀው እንዲወጡ ሲደረግም ተስተውሏል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው እጅግ ፍጥነት የተሞላው እርምጃ ሲሉ ንግግራቸውን ቀጥለዋል፡፡ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡