ድርቤ ወልተጂ በፊላደልፊያ ግራንድ ስላም ትራክ የሴቶች 800 ሜትርን አሸነፈች።
ድርቤ የቦታው ክብረወሰን በሆነ 1:58.94 ሰዓት በመግባት የውድድሩ ሻምፒዮን ሆናለች።
ድርቤ የፊላደልፊያ ግራንድ ስላም ሻምፒዮን ለመሆን የበቃችው በ1500 ሜትር ውድድር ላይም ድል ቀንቷት 24 ነጥብ በማግኘቷ ነው።
በጃማይካ ኪንግስተን የግራንድ ስላም ውድድር ለይም አሸናፊ የነበረችው ድርቤ ወልተጂ አጠቃላይ አሸናፊ ለመሆን በሚደረገው ፉክክር የሰበሰበችው ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።
የግራንድ ስላም ትራክ የመጨረሻ ውድድሮች ከሰኔ 27-29 2025 በሎስ አንጀለስ የሚደረግ ይሆናል፡፡