የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ከትራምፕ ጋር ጥሩ ስብስባ እንደነበራቸው አሳወቁ።
ዘለንስኪ እስካሁን ባለው ውይይት ደስተኛ እንደሆኑ ያሳወቁ ሲሆን ከእስካዛሬው ሁሉ እጅጉን ምርጡ ውይይት ብለውታል።
በእርግጥ ከሩሲያ በኩል የሚሰጡ ምላሾችንም መጠበቅ አስገዳጅ ሆኖ ተወስዱል።
የአውሮፓ መሪዎችም እጅግ ቁልፍ እና የማይነኩ ጉዳዮችን ለትራምፕ እንዳነሱላቸው አስታውሰዋል ዘለንስኪ።
የደህንነት ዋስትና፣ሰብዓዊ ድጋፍ ፣የእስረኛ ልውውጥ እና ሌሎች ጉዳዮች ለትራፕም ከዘለንስኪ እና አውሮፓ መሪዎች የተነሱ ጥያቄዎች ናቸው።
የግዛት ጉዳዮችን ግን ለሶስትዮሽ ውይይት ለፑቲን እናቆያቸዋለንም ብለዋል ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ።
ያም ሆኖ ግን ሩሲያ በዩክሬን ላይ ዛሬ ያደረሰችው የሰው አልባ አውሮፕላን እና ሚሳዔል ጥቃት ሌላ ውጥረትን አንግሱል።
በተጨማሪም ውይይቱ እየተደረገ ባለበት ሰዓት ማምሻውን በዩክሬን የአደጋ እየመጣ ነው ድምጽ ሰጭ ደውሎች (ሳይረንስ) ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ትርጉሙ አደገኛ ሆኖብናል ብለዋል ተንታኞች።
ኤን ቢ ሲ ኒውስ እንዳስነበበው።