የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫና ኢትዮ ፖስታ የስራ ስምምነት

Date:

የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የጽሁፍ አገልግሎትን በኢትዮ ፖስታ በኩል ማድረግ የሚያስችለውን ስምምነት ሰነድ ከወራት በፊት ከኢትዮጵያ ፖስታ ጋር ተፈራርሞ ነበር።

በስምምነቱ ወቅት የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ኪኒሶ ” ወደ ተቋሙ አገልግሎት ለማግኘት የሚመጡ ደንበኞች የሚፈልጉትን ውል የሚያጽፉት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አካባቢ የጽሁፍ አገልግሎትን የሚሰጡ ግለሶቦች ጋር ነው ይህም ተገልጋዮችን ለከፍተኛ ወጪ የሚዳርጋቸው ነበር ” ብለው ነበር።

ስምምነቱ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል የሚል ጥያቄ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያቀረበላቸው የኢትዮጵያ ፖስታ የማርኬቲንግ እና ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ማሙሽ በአምስት ቅርንጫፎች ስራው መጀመሩን አንስተዋል።

ዳይሬክተሩ ” የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት አቅራቢያ በግል ቢሮዎችን ተከራይተው የተለያዩ ክፍያዎችን እያስከፈሉ የውል እና የተለያዩ ሰነዶችን የጽህፈት ስራ የሚሰሩ ግለሰቦች የሚያስከፍሉት ክፍያ ተመጣጣኝ ካለመሆኑም በላይ የፕሮፌሽናሊዝም ችግር ይታይበታል ” ብለዋል።

የኢትዮ ፖስታ የማርኬቲንግ እና ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ማሙሽ በዝርዝር በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

” ከፌደራል ሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጋር የተፈራረምነው የሰነዶችን ዝግጅት ነው ማንኛውም ሰው ሰነዶችን ከማረጋገጡ በፊት የሰነድ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል ነገር ግን ከሰነድ ዝግጅት ጋር በተያያዘ ትልቅ የግንዛቤ ክፍተት ያለ በመሆኑ እሱ ክፍተት ከመሙላት አንጻር የድጋፍ አገልግሎት እንሰጣለን።

አንድ ተገልጋይ ሰነድ ለማዘጋጀት ሲፈልግ ጸሃፊዎች ጋር በመሄድ አጽፎ ይመጣል እዚህ ሂደት ላይ ከሚታዩ ትልቅ ችግሮች አንዱ የፕሮፌሽናሊዝም ችግር  ነው።

በጸሃፊዎች የሚዘጋጁ ዶክመንቶች ላይም ተመሳሳይ የሆነ የአከፋፈል ስርአት የለም በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የሰነዶች ማረጋገጫ እና የምዝገባ አገልግሎት ተቋማት አጠገብ ስራቸውን የሚያከናውኑ የጽህፈት አገልግሎት ሰራተኞች የተለያየ ክፍያን ያስከፍላሉ።

ይህንን ለማስቀረት ማህበረሰቡ መጠቀም በሚችልበት ደረጃ ከሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ጋርም በውይይት ዋጋ አስተያየት አድርገን በአምስት ቅርንጫፎች ላይ ስራችንን ጀምረናል።

በዋናው ፖስታ ቤት፣ በቦሌ መዳህኒአለም ፣ልደታ ፣ቤተል እና አራት ኪሎ ቅርንጫፎቻችን ላይ በአዲስ አበባ አራቱም መአዘን ያሉ ተገልጋዮችን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ የሰነዶች ዝግጅትን ጀምረናል።

የአገልግሎት ክፍያው እንደሚዘጋጀው የሰነድ አይነት ቢለያየም ለሰነዶች ዝግጅት ግን በአምስቱም ቅርንጫፎቻችን ተመሳሳይ ክፍያ ነው የምናስከፍለው።

ይህ አገልግሎቶች ሲሰፋ በተለያየ ቦታዎች ላይ በግል የሰነዶች የጽህፈት ስራ የሚሰሩ ዜጎችን ከስራ ውጭ አያደርግም ወይ ? የሚል ጥያቄ አንስተንላቸዋል።

ዳይሬክተሩ በምላሻቸው ” ሁሉም ማህበረሰቡን ማገልገል ወደ ሚችልበት ሲስተም መካተት ይኖርበታል በእኛ ቅርንጫፎች የሚሰሩ ስራዎች ይኖራሉ ፣አሁን የጽሑፍ አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎችን ስልጠና በመስጠት ከእኛ ጋር አብረው በሚሰሩበት ፣ተጠያቂነት በሰፈነበት፣ ማህበረሰቡን ተመሳሳይ ክፍያ በሚያስከፍሉበት መንገድ ላይ ሥልጠና በመስጠት አብረን የምንሰራው ስራ ይሆናል ” ብለዋል።

አክለውም ” ፍራንቻይዝ በምንለው መዋቅር ስር በአሁኑ ሰአት እነዚህን የጽህፈት ስራ የሚሰሩ ዜጎችን የመመልመል፣ የማነጋገር ፣ ቅስቀሳ የማድረግ እና መጥተው እንዲመዘገቡ የማድረግ ስራዎችን እየሰራን ነው የሆነ ቁጥር ላይ ሲደርስ ሥልጠና እንሰጣቸዋለን ከእኛ ጋር አብረው ይሰራሉ ” ነው ያሉት።

በተጨማሪም ” በአምስት ቅርንጫፎች ነው የጀመርነው በ 2018 ዓም መጀመሪያ አካባቢ በሙሉ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ላይ ሁሉም ሰው አገልግሎቱን በቅርብ ርቀት ላይ በሚያገኝበት ሁኔታ የጽህፈት አገልግሎቱን ለመስጠት እየሰራን ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።

” የጽህፈት አገልግሎቱን በሦስት አይነት መንገዶች እንሰጣለን በራሳችን የፖስታ አገልግሎት ቢሮዎች ፣ በሰነዶች ማረጋገጫ አቅራቢያም ቢሮዎችን እየተከራየን፣ አሁን የጽህፈት ስራ እየሰሩ ያሉ ወገኖችን ደግሞ አቅፎ በመያዝ ከእነሱ ጋርም አብረን እንሰራለን ” ብለዋል።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል፡፡ በሥርዓተ...

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስክሬን ሽኝት በሚሊንዬም አዳራሽ ተካሂዷል

የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ታየ አጽቀስላሴ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት...

ሸህ ዑመር ገነቴ!!!

እንዲህ ወደ ደገር…እንዲህ ወደ ገታ…ደግሞም ወደ ዳና፤ጫሌ ገንደጎራ፤የተሰየማችሁ፤ሰው መሆን…..ሰው...