የ12ኛ ክፍል መልቀቂያን ከ500 በላይ ላመጡ ተማሪዎች ማበረታቻና እውቅና ተሰጠ

Date:

በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ500 በላይ ውጤት ካስመዘገቡ 1321 ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት ላመጡ 336 ተማሪዎች እውቅና መስጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

በ2016 የትምህት ዘመን የ12ኛ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 21.3 በመቶ የሚሆኑት የማለፊያ ነጥብ ያመጡ ናቸው። በ2017 ያለፉ ተማሪዎች ወደ 31 በመቶ ጨምረዋል።

እንዲሁም እንደ ሀገር 100 ፐርሰንት ካሳለፉ 50 ትምህርት ቤቶች 17ቱ በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ናቸው ተብሏል።

በተጨማሪም ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች 100 ፐርሰንት ማሳለፍ መቻላቸው የስራችን ውጤታማነት ማሳያ ነው።

በእውቀናና ማበረታቻ መርሀ ገብር ላይ የተገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ “ዛሬ የማበረታቻ ሽልማት ከሰጠናቸው መካከል አይነ ስውራን እና መስማት የተሳናቸው ተማሪዎቻችን ለገጠማቸው የአካል ጉዳት ፈተና እጅ ሳይሰጡ ላስመዘገቡት ከፍተኛ ውጤት ትልቅ ክብር አለኝ” ብለዋል።

አያይዘውም፣ “የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ውድ ተማሪዎቻችን በዩኒቨርሲቲዎቹ የሚኖራችሁ ቆይታ የበለጠ እውቀት የምትቀስሙበት፣ ለአገር ለወገን የሚጠቅም ክህሎት ይዛችሁ የምትወጡበት እንዲሆን እመኛለሁ።” ነው ያሉት ከንቲባዋ።

መረጃው የከንቲባ ጽ/ቤት ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ...

ትራምፕ ከጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በንግድ እና ወሳኝ ማዕድናት ላይ ንግግር አደረጉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማክሰኞ እለት የጃፓን የመጀመሪያዋ...

ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ እና ተግባረ-ዕድ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

በትራንስሽን ማኑፋክቸሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማ ባለቤትነት የተያዘው ኢንፊኒክስ እና የአዲስ አበባ...

አንዳንድ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በአባይ ወንዝ እኔ ብቻ ልጠቀም የሚለው አቋማቸው እንደከሸፈ ሊገነዘቡ ይገባል

ታላቁ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብን በመቀልበስ የተፋሰሱን...