ድምጻዊ ይሁኔ ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ እውቅና ተሰጠው

Date:

“ፍኖተ ጥበብ” በሚል ርዕስ የሕይወት ልምዱንና ግለ ታሪኩን የከተበበትን መጽሐፍ ለማስመረቅ በባህር ዳር ከተማ የተገኘው ተወዳጁ ድምጻዊ ይሁኔ በላይ፣ ለባህላዊ  ሙዚቃ እድገት ላበረከተው ጉልህ አስተዋጽኦ በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡

ከዩኒቨርስቲው በተጨማሪ የአገው ፈረሰኞች ማህበርም ለአርቲስት ይሁኔ የክብር ሽልማት ሰጥቶታል፡፡

ድምጻዊ ይሁኔ በላይ ከግሽ ዓባይ የኪነት ቡድን ጀምሮ በርካታ የባህል ሙዚቃ ሥራዎችን ያበረከተ አንጋፋ ድምጻዊ ነው፡፡

አርቲስቱ የቱሪስት መዳረሻዎች እንዲተዋወቁ  ለጉዛራ ቤተ መንግስትና ለዘንገና ሐይቅ አቀንቅኗል፡፡   በዓላት በድምቀት እንዲከበሩም  ለአገው ፈረሰኞች በዓል፣ ለጥምቀትና ለዘገሊላ ዘመን የማይሽራቸውን ሥራዎች ማበርከቱ ይታወቃል፡፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢመማ 23ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ እና በአዳማ ከተሞች ተካሔደ

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 23ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻው ሥነ_ሥርዓት...

ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ...