…
ጀንቦሮ ሪል እስቴት በ 5 ዓመታት ውስጥ 4ኛው የሆነውን የአፓርትመንት ፕሮጀክት በድምቀት አስመርቆ ፤ ሰማንያ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችና አርባ የንግድ ሱቆች በድምሩ አንድ መቶ ሃያ ቤቶችን ለገዥዎች አስረክቧል።
ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ/ም በቦሌ ቡልቡላ ሳይት በተከናወነው በዚህ ደማቅ መርኅግብር ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶችና የድርጅቱ ደምበኞች የተገኙ ሲሆን የቁልፍ ርክክብ ተካሂዷል፡፡
የጀንቦሮ ሪል እስቴት ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ዮናስ ብርሀኔ ፤ ፕሮጀክቱን ገንብቶ ለማጠናቀቅ 2 አመት ከ 6 ወራት ጊዜ ብቻ እንደወሰደ ገልጸው ድርጅቱ ለኮንስትራክሽን ስራው ግብዓት የሚያቀርቡ የኮንክሪት ሚክስ፣ የአሸዋ እና ጠጠር አምራች እህት ኩባንያዎችን አቋቁሞ የሪል እስቴት ስራውን እንዲደግፉ ማድረጉ በ 5 አመታት ውስጥ 4 የአፓርትመንት ፕሮጀክቶችን ከተዋዋለበት ጊዜው አስቀድሞ ገንብቶ ለደምበኞቹ በፍጥነት ለማስረከብ እንዳስቻለው ገልጸዋል፡፡
ኢ/ር ዮናስ አክለውም ፤ ጀንቦሮ በሪል እስቴት ገበያው በፍጥነትና በጥራት በመስራት፣ በወቅቱ በማስረከብ ፣ በገበያው ዕጅግ ታማኝና ተመራጭ ብራንድ መገንባት መቻሉን ገልጸው ድርጅቱ የሚታወቅበትን “በጊዜ ግቡ!” የሚለውን መሪ ቃል በጊዜ በመገንባትና በጊዜ በማስረከብ ደምበኞችም በጊዜ ወደቤታቸው እንዲገቡ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል::
ድርጅቱ በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ኢንደስትሪን ማርሽ ቀያሪ የሆነ በሺህ የሚቆጠሩ አፓርትመንቶችን ከአመት ባነሰ ጊዜ ገንብቶ ማስረከብ የሚችል የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የግዥ ሂደት ማጠናቀቁን
በ2018 ዓ/ም ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ያሳወቁት ኢ/ር ዮናስ ጀንቦሮ በአሁኑ ወቅት በቦሌ ቡልቡላ እና በሳርቤት ቫቲካን ግዙፍ የአፓርትመንት ፕሮጀክቶች ግንባታ እና ሽያጭ በሚያስደንቅ ፍጥነት እያከናወነ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው የገዙትን ቤት ቁልፍ የተረከቡት ደንበኞች ያለምንም ተጨማሪ እንግልት ፤ ጃንቦሮ ሪል እስቴት ቃሉን አክብሮ የቤት ባለቤት ስላደረጋቸው አድናቆታቸውን ገልፀዋል።