ግሎባል ጀነራል ኮንስትራክሽን ሐምሌ 27/2017 ዓ.ም በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል የ2017 የስራ እንቅስቃሴውን ከድርጅቱ ሰራተኞች ጋር በመሆን ገምግሟል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ከድር ሐሰን “የጥራት ጉዳይ የእኛ የመጀመሪያ መስመራችን ነው፣ ማንም ሰው ጥራት ላይ እንዲደራደር አንፈቅድም” ብለዋል።
አክለውም ድርጅቱ በኮንስትራክሽን ዘርፍ በክልል, በአዲስ አበባ እና ከፌደራል ተቋማት ጋር ለሚሰሩት ፕሮጀክቶች ላሳየው የላቀ ለውጥ እና እድገት የእያንዳንዱ የድርጅቱ አባላት አስተዋጾ ከፍተኛ በመሆኑ በ2017 ዓ.ም ላሳየው መልካም የሥራ አፈፃፀም ለድርጅቱ ሠራተኞች የእውቅና ፕሮግራም መዘጋጀቱን ገልጿል።
እውቅና ያገኙ ሰራተኞች ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ያሳዩ ናቸው ተብሏል።
ግሎባል ጀነራል ኮንስትራክሽን በፕሮጀክቶቹ ለበርካታ ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠር ችሏል።