“ጦርነቱ አብቅቷል” ትራምፕ

Date:



የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛው ጦርነት አብቅቷል ፣ መካከለኛው ምሥራቅም ወደ መደበኛ ሁኔታው ​​ይመለሳል” ሲሉ ተናገሩ ።

ትራምፕ ይሄንን ያሉት እስራኤልና ሐማስ ታጋቾችንና እስረኞችን ለመልቀቅ እየተጠባበቁ ባሉበት ወሳኝ ወቅት ነው።

ለሁለት አመታት የዘለቀውን የጋዛ ጦርነት ለመቋጨት በአሜሪካ በቀረበው የሰላም ስምምነት እቅድ መሰረት  የመጀመሪያው ምዕራፍ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን  ተከትሎ ትራምፕ ወደ እስራኤል አቅንተዋል።

ትራምፕ በፕሬዚዳንት በአውሮፕላን (Air Force One) ላይ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንደሚጸና ያላቸውን እምነት ገልጸው፣ እንዲሁም የሰላም ቦርድ የተባለ ዓለም አቀፍ አካል በቅርቡ እንደሚቋቋም አስታውቀዋል።ፕሬዚዳንቱ  የሰላም ስምምነቱ እንዲሳካ ላደረጉት ጥረት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን እና ቁልፍ ሚና የተጫወተችው ኳታርን አድንቀዋል።

በስምምነቱ የመጀመሪያ ምእራፍ መሰረት ሐማስ የቀሩትን ታጋቾች ለመልቀቅ የተዘጋጀ ሲሆን በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ እኩለ ቀን ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል ። እስራኤልም በተመሳሳይ ወደ 2,000 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን እስረኞችን የምትለቅ  ይሆናል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ እስራኤል እንደደረሱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በሀገሪቱ ፓርላማም ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው ።

ትራምፕ ከእስራኤል ጉብኝት በኋላ ጦርነቱን በዘላቂነት ለማስቆም በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ግብፅ ሻርም ኤል ሼክ ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዘገባው የቢቢሲ  ነው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የህዳሴ ግድቡ ውዝግብ በፖለቲካዊ ሳይሆን በቴክኒካዊ መንገድ መፈታት አለበት

በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ፣ እና የመካከለኛው ምስራቅ...

የ7 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ አለመከናወኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሚተዳደሩ 7 የጋራ መኖሪያ...

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ በ80 ዓመታቸው ከዚህ...