በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
የሪሚዲያል ፕሮግራም #የማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች ፦
1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
2. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
3. አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
4. ሲቪል ሰርቪርስ ዩኒቨርሲቲ
5. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
6. ጅማ ዩኒቨርሲቲ
7. ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ናቸው።
ተማሪዎች የሞሉትን ምርጫ በ student.ethernet.edu.et በኩል ማረጋገጥ የሚችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡