15 አዲስ የተከፈቱት ቅርንጫፎች ቀጣይ ዓመት ሥራ ይጀምራሉ ተብሏል

Date:




በአገልግሎቱ ላይ የሚነሳበትን ቅሬታ ለመፍታት ላለፉት 4 ዓመታት የሪፎርም ሥራዎችን ሲሰራ የቆየው የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 34 ነጥብ 1 ቢልዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡ 

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት “አገልግሎት አሰጣጡን ከእጅ ንክኪ ነጻ በሆነ መንገድ ለመስጠት የሚያስችል የሪፎርም ሥራ ተሰርቷል” ብለዋል።

“ተቋሙ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጡን በክልሎችም እያስፋፋ ነው” ያሉም ሲሆን፤ ዋነኛ አላማውም ዜጎች ያለምንም ተጨማሪ እንግልትና ወጪ በአቅራቢያቸው በሚገኝ ቅርንጫፍ ቢሮ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ እንደሆነ ለአሐዱ ገልጸዋል።

የተቋሙ የፓስፖርት አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ታደሰ በበኩላቸው፤ ፓስፖርት ለማውጣት የልደት ካርድ እና ዲጂታል መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያለ ቅድመ ሁኔታ አገልግሎት እንደሚያገኝ ተናግረዋል።

ማህበረሰቡ ባለማወቅ ከሕገ-ወጥ ደላሎች ጋር በመነጋገር አላስፈላጊ ድርጊት እንደሚያደርጉበት ሁኔታ መኖሩን አንስተው፤ “ከዚህን መሰል ድርጊት እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል” ሲሉ አሳስበዋል።

በተቋሙ በተቀመጠው አሰራር መሠረት ከመደበኛ እስከ አስቸኳይ አገልግሎቱ እንደሚሰጥ የገለጹም ሲሆን፤ ሕብረተሰቡ ሁለቱን አማራጭ በመጠቀም አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል።

አገልግሎቱን ለፈለጉ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ተደራሽ ለማድረግም 15 ቅርንጫፎች የተከፈቱበት ሁኔታ መኖሩን አንስተው፤ “እነዚህ አዲስ የተከፈቱት ተቋማት ቀጣይ ዓመት ሥራ ይጀምራሉ” ብለዋል።

እነዚህ 15 ተቋማት ከክልል ከተሞች ርቀው የሚገኙ ከተሞች ላይ መከፈታቸውን የገለጹም ሲሆን፤ ይህም ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አስታውቀዋል።

ለተቋሙ ችግር የሆነው በሕገ-ወጥ መንገድ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ተገልጋዮች መበራከታቸው መሆኑን አንስተው፤ ይህን ተግባር የሚፈፅሙ ሰዎችን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን የቁጥጥር ሥራ እየተሰራ መሆኑን ለአሐዱ ገልጸዋል።

አክለውም በሕገ-ወጥ መንገድ የልደት ካርድ የሚያወጡ እና ፎርጂድ ማስረጃዎችን የሚያወጡ ግለሰቦች ለተቋሙ ችግር እንደሆነበት አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ዕጣ ፈንታቸው ወደ ኤሌክትሪክ መቀየር ነው

በነዳጅ የሚሠሩና አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ተሽከርካሪዎች ዕጣ ፈንታቸው ወደ...

የማሌዥያ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ኤምባሲ ከ43 ዓመታት በኋላ ተከፈተ

ማሌዥያ በአዲስ አበባ የነበራትን ኤምባሲ ከ43 ዓመታት በኋላ ዳግም...

ህጻናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ተመረቀ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚሰሩ የልማት ሥራዎች ሁሉ ኪነ...

ትራምፕ ውሸታም ናቸው- የኮንግረስ አባል ኢልሀን

የኮንግረስ አባል ኢልሀን ኡመርና የፕሬዝደንት ትራምፕ ውዝግብ እንደቀጠለ ነው፡፡...