20ኛው የዓለም ሥራ ድርጅት በአፍሪካ ህብረት እየተከበረ ነው

Date:

ኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን መሠረተ ልማት የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ በዘላቂነት የሚያሻሽል ውጤት እያስመዘገበች መሆኗን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገለጹ።

20ኛው የዓለም ሥራ ድርጅት በሥራ ላይ የተመሠረተ የባለሙያዎች ሌቨር ቤዝድ ፕራክቲሽነርስ አህጉራዊ ስብሰባ “የማይበገር ማኅበረሰብ እና ጤናማ አካባቢ፤ የሰው ኃይልን በብዛት የሚጠቀሙ የኢንቨስትመንት ፕሮግራም አካሄዶች” በሚል መሪ ሐሳብ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው።

ሚኒስትር ጫልቱ በዚህ ወቅት፤ ስብሰባው የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ ድህነት ቅነሳንና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሐሳቦች በማፍለቅ የጋራ አንድነት እና ቁርጠኝነት የምናሳይበት ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ለሥራ ፈጠራ ችግር ከሆኑት መካከልም፤ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የቴክኖሎጂ አቅም ልዩነት፣ ጂኦ ፖለቲካዊ ግጭት ተጠቃሽ ናቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ ከዓለም የሥራ ድርጅት ጋር በቅርበት እንደምትሠራ ገልጸው፤ መንግሥት ለሥራ ፈጠራ፣ ለዘላቂ ልማት፣ የማይበገር ማኅበረሰብ ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በተለይ በመንገድ መሠረተ ልማት ላይ ትኩረት በማድረግ ከሥራ ዕድል ባለፈ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ግቦችን ለማሳካት በመንግሥታት፣ በትምህርት ተቋማት እና በግሉ ዘርፍ መካከል ትብብር መፍጠር እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር÷ ስብሰባው አፍሪካውያን ፖሊሲ አውጭዎችና ባለሙያዎች ፈጠራን መሰረት ያደረገ ስራ ለመፍጠር፣ ድህነትን ለመቀነስና አየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

አላማውን ለማሳካትም በአህጉሪቱ የሁሉም ሀገራት የጋራ ጥረት ያስፈልጋል ያሉት አፈ ጉባዔው ÷  ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊና ቀጣናዊ ጥረት እንዲሁም ብሔራዊ የድርጊት መርሐ ግብር ለንግድና ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ነው ያሉት፡፡

ፖሊሲዎች፣ የልማት ስትራቴጂዎች እንዲሁም የመሰረተ ልማት ሃብቶች ለስራ እድል ፈጠራና ለአካታች ለውጥ መሰረት መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የልማት ግቦች ድህነትን ለመቀነስ፣ የሥራ እድል ለመፍጠርና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ማረጋጥ የሚያስችሉ እንደሆነ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዓለም ሥራ ድርጅት አህጉራዊ ሥብሰባ የአህጉሪቱን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት የጋራ መፍትሔ የማስቀመጥ ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አፍሪካ ያሉባትን ፈተናዎችና ያሏትን መልካም እድሎች በአግባቡ ለመጠቀም በትብብር ላይ የተመሰረተ የተግባር ድርጊት ያስፈልጋል ሲሉም አመልክተዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የስደትና መፈናቀል ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል

በተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እና ፕሬዚዳንት አልሲሲ ፊት ለፊት ሊገናኙ?

አብይ አህመድ እና አበዱልፈታህ አልሲሲ ፊትለፊት እንዲገናኙ እንደምትፈልግ አሜሪካ...

በትግራይ ጦርነትን ከማስቀረት ሰሞኑን እየተካሄዱ ያሉት ሰልፎች መበረታት አለባቸው

ላለፉት ተከታታይ ቀናት በርካታ ጥያቄዎችን ያነገቡ የቀድሞ ተዋጊዎች በትግራይ...

ግብፅ እና ሱዳን በዓባይ ውኃ እና በሱዳን ቀውስ ዙሪያ ተወያዩ

የግብፁ ፕሬዝደንት ዐብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር...