ኢትዮጵያ ጦርነት ልትከፍትብኝ እየተዘጋጀት ነው ስትል የከሰሰቻት ኤርትራ፤ ክሱን “ወታደራዊ ጠብ አጫሪነት” ስትል ውድቅ አደረገች።
የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል፤ «የቀድሞ ግዛትን ለማስመለስ ያለመ” ያሉትን ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ፣ ወታደራዊ የጠብ አጫሪነት የታከለበት ነው ሲሉ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉተሬቭ በላከው ደብዳቤ አስመራ ፣ ፅንፈኛ ካለው የህወሓት አንጃ ጋር ኢትዮጵያን ለመውጋት እየተዘጋጁ ነው ሲል ከሷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞትዮስ የፈረሙበት ይህ ደብዳቤ፤ የፌደራል መንግሥት ወታደሮች ከአማጽያን ጋር በሚዋጉበት በአማራ ክልል «ሁለቱ አካላት የታጠቁ ቡድኖችን ይደግፋሉ፣ ያንቀሳቅሳሉ ይመራሉም” ሲልም ይወቅሳል።