ስቲሊ አር.ኤም.አይ ላለፉት አራት ዓመታት የፕላቲኒየም ሸልማት ተሸላሚው

Date:

የ2017 በጀት ዓመት 7ኛው የታማኝ ግብር ከፋዮች ዕውቅና እና ሽልማት በቅርቡ የተካሄደ ሲሆን 105 ግብር ከፋዮች በፕላቲየም ደረጃ፣ 245 በወርቅ ደረጃ እንዲሁም 350 ግብር ከፋዮች ደግሞ በብር ደረጃ በድምሩ 700 ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት አግኝተዋል፡፡

በተጨማሪም ባለፉት አራት የግብር ከፋዮች እውቅና በተከታታይ የፕላቲኒየም ተሸላሚ የሆኑ 30 ግብር ከፋዮች ልዩ ተሸላሚዎች ሆነዋል፡፡

በዚሁ መርሃ-ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግሥት ለግብር ከፋዮች ቃል በገባው መሰረት በገቢው ዘርፍ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥነትን ለመከላከል የተለያዩ በቴክኖሎጂ የተደገፉ አሰራሮችን እውን አድርጓል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ለሀገር የታመኑ ግብር ከፋዮችን ለማበረታታት በፕላቲየም ደረጃ ዕውቅና እና ሽልማት ለተበረከተላቸው ድርጅት ባለቤቶች ወይም ሥራ አስፈጻሚዎች ዓለማቀፍ ሥራቸውን ቀላል ያደርግላቸው ዘንድ ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እንደሚሰጣቸው መወሰኑ የሚታወቅ ነው፡፡

ስቲሊ አር.ኤም.አይ ኃላ.የተ.የግ.ማህ ከ 30ዎቹ ልዩ የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ዉስጥ አንዱ ሊሆን ችሏል፡፡

ከዚህም በተጨማሪም ሰባት የሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ድርጅቶች በተለያየ ደረጃ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

ላለፉት አራት ዓመታት በታማኝነት የፕላቲኒየም ሸልማት ካገኙት 30 ልዩ ተሸላሚዎች ዉስጥ ስቲሊ አር.ኤም.አይ ኃላ.የተ.የግ.ማህ አንዱ በመሆንና መንግስት በሚሠጠዉ ማበረታቻ እና ድጋፍ ከኢትዮጵያ ውጭ በተመረጡ የአፍሪካ ሀገራት ኢንቨስት እንዲያደርግ ጥሪ እንደቀረበለት ተቋሙ አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የህዳሴ ግድቡ ውዝግብ በፖለቲካዊ ሳይሆን በቴክኒካዊ መንገድ መፈታት አለበት

በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ፣ እና የመካከለኛው ምስራቅ...

የ7 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ አለመከናወኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሚተዳደሩ 7 የጋራ መኖሪያ...

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ በ80 ዓመታቸው ከዚህ...