የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የሰራዊት አባላት ተጠቃሚ የሚያረጋግጥ ደንብ ማጸደቁ አስታውቋል

Date:

እሁድ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም የጀመረው የትግራይ ኃይል ሰልፍና ተቃውሞ ዛሬ ቀጥሎ ከእንዳስላሰ-ሽረ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋና ተምቤንና ሌሎች አከባቢዎች ወደ መቐለ የሚያስገባ መንገድ ተዘግቶ ውሏል።

ይህንን ተከትሎ ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ የፅሁፍ መግለጫ ያወጣው የጊዚያዊ እስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ካቢኔ ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ያወጣው የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ረቂቅ ደንብ ዛሬ ማፅደቁን አመልክተዋል።

ካቢኔው በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባው  የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ደንብ በዝርዝር ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

የፀደቀው ደንብ ፦

  • መሰረታዊ ፍላጎቶች
  • የህክምና አገልግሎት
  • የቤት መስሪያ መሬት
  • በመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚሰጥ የክብር አገልግሎት
  • ትምህርት ስልጠናና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ያካተተ ነው ብሏል ከፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት የተሰጠው የፅሁፍ መግለጫ።

” የፀደቀው የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች ተጠቃሚነት ደንብ ለረጅም ጊዜ ጥናት የተደረገበት ከፀጥታ አመራሮች ውይይት ሲካሄድበት የቆየ ነው ” ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብሮች

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ። ዛሬ ሰባት...

ለዩክሬን ሰላም ‘በጣም ተቃርበናል’ ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬኑ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በትናንትናው...

በዲማ የአለባበስ ቅጣት

በጋምቤላ ክልል ዲማ ከተማ ከባህል ውጪ በሆነ አለባበስ ምሽት...