የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማውን ኀዘን ገልጿል፡፡
ምክር ቤት ባስተላለፈው የሀዘን መግለጫ፤ የሀገራችን ዋርካ እና የሁሉም አባት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ወደ አኼራ ሄደዋል ብሏል።
ህልፈታቸው የመላው ሀገራችን ህዝብ ሀዘን ነው ሲልም ምክር ቤቱ ገልጿል፡፡
እኚህን ታላቅ አባት ላበርክቷቸው ሀገራዊና ሃይማኖታዊ አስተዋፆ በሚመጥን መልኩ ስርዓተ ቀብራቸው በመንግስት ደረጃ ኢስላማዊ ስነ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ኃላፊነቱን በመውሰድ የሚፈፅም መሆኑን አስታውቋል፡፡
ሀገራችን ታላቅ አባት አጥታለች ያለው ምክር ቤቱ፤ ሀዘናችን መሪር ቢሆንም የአላህን ውሳኔ ከመቀበል ውጪ አማራጭ የለም ሲል የሀዘን መግለጫ መልእክቱን አስተላልፏል።