የሙፍቲ ቀደምት ፎቶግራፍ

Date:

ይህ ፎቶግራፍ የተነሳው በ1965/1966 ሲሆን በፎቶው የሚታዩት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ጉባኤ መስራች አባቶች ናቸው። በታችኛው ረድፍ ላይ ቆመው ከሚታዩት አባቶች መካከል (ከግራ ወደ ቀኝ) የመጀመሪያው ሰው (ጥቁር መነጽር ያደረጉት) የገለምሶው ሓጂ አሕመድ ኑሬ ናቸው።

ሐጂ አሕመድ በወቅቱ የፓርላማ አባል ነበሩ። ሶስተኛው ሰው ዛሬ ያረፉት ሙፍቲ ሓጂ ዑመር ኢድሪስ ናቸው። መሃል ያሉት ታዋቂ ዓሊምና ቁርኣንን በአማርኛ ከተረጎሙት ሰዎች አንዱ የሆኑት ሓጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ ናቸው።

ዛሬ ስለሙፍቲ ሓጂ ዑመር ተጽፎ ያነበብኩት አንድ ጽሑፍ ዕድሜአቸው 86 ዓመት እንደሆነ ያትታል። ይህ መረጃ ትክክል አይመስለኝም።  ይህንን ፎቶ ስናይ ዕድሜአቸው ከዚያ ያለፈ እንደሆነ በትክክል ይገባናል። እኔ ራሴ ሙፍቲን ካወቅኳቸው ሰላሳ ዓመት ሆኖኛል። ያኔ ሳውቃቸው ገጽታቸው ከአሁኑ ብዙም የተለየ አይደለም።


(“በዚህ ፎቶ ውስጥ የሚታዩት ዓሊም ሌላ ሰው ናቸው” ካልተባለ በስተቀር የሙፍቲ ዕድሜ በዘጠናዎቹ ውስጥ እንደሆነ ነው የማምነው)።
ከአፈንዲ ሙተቂ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል፡፡ በሥርዓተ...

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስክሬን ሽኝት በሚሊንዬም አዳራሽ ተካሂዷል

የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ታየ አጽቀስላሴ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት...

ሸህ ዑመር ገነቴ!!!

እንዲህ ወደ ደገር…እንዲህ ወደ ገታ…ደግሞም ወደ ዳና፤ጫሌ ገንደጎራ፤የተሰየማችሁ፤ሰው መሆን…..ሰው...