የህብረት ስራ ማህበራት ባክኖ የነበረ 1.6 ቢሊየን ብር ማስመለስ ተችሏል አሉ

Date:

ሌሎችም በርካታ ውጤቶች በኀብረት ሥራ ማህበራት የሪፎርም ስራ መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሺሰማ ገብረሥላሴ ተናግረዋል።

ለአብነትም ማህበቱን በማዋሀድ፣ በማፍረስና ማጠናከር በተሰራው ስራ ከ120 ሺህ በላይ  የነበረው የኀብረት ሥራ ማህበራት ቁጥር አሁን ላይ ወደ 89 ሺህ ዝቅ ማለቱን ጠቅሰዋል።

የአመራር ስርአታቸውን ለማሻሻል በተሰራው ስራም ከ6900 መሰረታዊ ማህበራትና 57 ዩኒየኖች የአመራር ለውጥ አድርገዋል ያሉት አቶ ሺሰማ ወደ 4300 የሚሆኑ ሴቶችና ወጣቶች በአመራርነት እንዲካተቱ መደረጉንም ተናግረዋል።

አዳዲስ አባላትን በማፍራት የኀብረት ሥራ ማህበራት ዓመታዊ ካፒታል የማፍራት አፈፃፀማቸውን እንዲያሳድጉ እና  የቁጠባ መጠን እንዲጨምሩ ማድረግ መቻሉንም አመልክተዋል::

በከተሞች የምርት አቅርቦትና ግብይት ላይ በተሰራው ስራም በሀገር አቀፍ ደረጃ 378 ኀብረት ስራ ማህበራት ከ1400 በላይ በሚሆኑ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች ተሳትፈው ዋጋ እያረጋገጡ ይገኛሉ ብለዋል።

12ኛው የኅብረት ሥራ ማህበራት ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚየም ከጥር 26 እስከ 30 ቀን 2018  በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልና በአድዋ ድል መታሰቢያ እንደሚካሄድ ተነግሯል።

“ኅብረት ሥራ ከምርት እስከ ግብይት፤ ከአምራች እስከ ሸማች” በሚል መሪ ሃሳብ በሚዘጋጀው ኤግዚቢሽን እና ባዛር ላይ 360 የሚሆኑ የኅብረት ሥራ ማህበራት ይሳተፋሉ ተብሏል።

ማህበረሰቡ ለዕለት ተዕለት ፍጆታው የሚጠቀምባቸው ከ22 ሺህ ኩንታል በላይ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ይቀርቡበታል የተባለ ሲሆን ፤ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ቀጥታ ግብይት ይፈጸማል ተብሎ እንደሚጠበቅም ኮሚሽኑ የላከን መረጃ ያመለክታል።

ንጋቱ ረጋሳ (ሸገር 102.1)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሜሪካ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አየር ወለዶቿን መላኳን አረጋገጠች

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ፔንታገን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የእግረኛ እና...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር የሚደረግን ውይይት ውድቅ ማድረጓ ጥልቅ አለመተማመን እንዳለ ያሳያል

ዋሺንግተን ንግግር እየተደረገ መሆኑን ስትገልጽ ቴህራን በበኩሏ ወዲያውኑ ውድቅ...

የቀድሞዋ ርዕሰ ብሔር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የፎርብስ የሕይወት ዘመን ትጋት ተሸላሚ ሆኑ

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ በደቡብ አፍሪካ...