የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 4 ቢልየን ብር ወጪ 22 ፕሮጀክቶችን አስመረቀ

Date:


ምረቃው የተደረገው የዩኒቨርሲቲው 70ኛ ዓመት ምስረታና 100ኛ ዓመት የማስተማሪያ ሆስፒታል የሆነበትን በዓል ምክንያት በማድረግ ነው።

የካንሰር ጨረር ህክምና ማዕከል፣ ንፁህ የመጠጥ ውሃ፣ የህክምና ኦክስጅን ማምረቻ ማዕከልን ጨምሮ ዩኒቨርሲቲው ሲገነባቸው የነበሩ ሌሎች 22 ፕሮጀክቶች ናቸው የተመረቁት።

ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገርና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በምረቃው ላይ ተገኝተዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የማስተማርያ ሆስፒታል ከአካባቢው ሰዎችን ከማከም ባለፈም የህክምና ባለሙያዎች እንደ ሃገር እንዲፈሩ አድርጓል፣ ይህም ስራ በተሻለ መንገድ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች እውቀትን ሲያስተላልፉ ያሉበትን ማህበረሰብ ማዕከል ማድረግ አለባቸው፣ ጎንደር የዕውቀት ማዕከል ናት ፣ነባር ዩኒቨርስቲው ነባሩን እውቀት በተሻለ መንገድ እንዲሰፋ ማድረግ ያስፈልጋል  ሲሉ ጠቅሰዋል።

ዩኒቨርስቲው ዋንኛ አላማው ሊሆን የሚገባው ተወዳዳሪና ጥራት ያለው የሰው ሃይል በዕውቀት መፍጠር ላይ ሊበረታ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን(ዶ/ር) ኡሁን የተመረቁ ፕሮጀክቶች ዩንቨርስቲው ራስ ገዝ ለመሆን በሚያደርገው ስራ አጋዥ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በጎንደርና በአካባቢው የካንስር ታካሚዎች የጨረር ህክምና ለማግኘት ወደ አዲስ አበባ ፣ ጅማ እና ሀዋሳ ለመሄድ ይገደዱ ነበር ተብሏል።

አሀን የተመረቀው የካንሰር ጨረር ህክምና ማዕከል እንደ ሃገር 5ተኛ ማዕከል ሲሆን በአማራ ክልል ደግሞ ብቸኛ መሆኑን ሰምተናል።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ጎንደር ከተማ ከሚያቀርበው የውሃ አቅርቦት ወደ 20 ከመቶ ይወስድ ነበር የተባለ ሲሆን የተመረቀው የውሃ ፕሮጀክት ዩኒቨርስቲው የውሃ ፍላጎቱን በራሱ አቅም እንዲችል ያደርገዋል ተብሏል።

የፍሳሽ ቆሻሻን በተገቢው መንገድ አክሞ  ለአትክልት ውሃ ማጠጣትና ለሌሎች አገልግሎቶች እያዋለ ሲሆን ለንፁህ የመጠጥ ውሃ ለመጠቀም ዩንቨርስቲው ማቀዱን ተናግሯል።

ከተመረቁት ፕሮጀክቶች ውስጥ 17 የሚሆኑት አዲስ የተገነቡ ሲሆን ቀሪዎቹ ነባር መሆናቸውን ሰምተናል።

ሃያዎቹ ፕሮጀክቶች በመንግስት በጀት 2ቱ ደግሞ በአጋር አካላት ድጋፍ የተገነቡ ናቸው።

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሙፍቲ ቀደምት ፎቶግራፍ

ይህ ፎቶግራፍ የተነሳው በ1965/1966 ሲሆን በፎቶው የሚታዩት የኢትዮጵያ እስልምና...

አገር ጥቁር ትልበስ!

ቃለ መጠይቅ የማድረግ እድል ሳገኝ ኢቲቪ ገብቼ ዓመትም አልሆነኝ።...

ታላቅ አረጋዊ ፣ የበሳል አእምሮ ባለቤት፣ አገርን የሚወዱ…

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት...

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን ሽኝት እየተደረገለት ነው

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን ከመኖሪያ ቤታቸው...