ሀገር ይኖርህ ዘንድ ትሻለህ?

Date:

አብነት  ሲራጅ

ሰው ሆኖ በሀገሩ ለዛውም ዕትብቱ በተቆረጠበት ሰፈር እና መንደር ሰላምን፤ ዕድገትን፤ መበልፀግን እና ልማትን  የማይሻ ፍጥረት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ አንዱም ከሌላው ተሻሽሎ እና ተለውጦ መኖርንም የሚጠላም እንደዛው፡፡ ከዚህ ሻል ሲል ደግሞ ውብ እና ያማረች ሀገር ውስጥ የሚጠላም ፍጡር አለመኖሩ ገነት ወይም ጀነትን መናፈቁ እውነታውን ያስረግጥልናል፡፡

የሰው ልጅ በተፈጥሮ ፀጥ ረጭ ያለ ንፁህ አየር እና ምቾት ያለውን ሥፍራ ይሻል፡፡ ይህ ማለት እንደ አንድ ሀገር እንኳን ብንመለከት ከአንዱ ሥፍራ እንደሚያገኘው ምቾት እና ሰላም እንደ ማለት ነው፡፡

ማንኛውም የሰው ልጅ ስሜቱን፤ ማንነቱን እና ክብሩን በሚነካ ተመሳሳይም ሆነ ሊመሳሰለው ከማይችል ፍጥረት ጋር መኖርም ሆነ መደራደር አይሆንለትም፡፡ ይባስ ለራሱ ያጣውን ሰላም የወረሰውን መጥፎ ባሕሪ ለሌላው እያዛመተ በሽታውን ሲዘራ ሊኖር ይችላል፡፡ ይህ ታድያ ሀገርን ትርጉም አልባ የከንቱ ፍጠራታትም መኖርያ ተደርጋ እንድትሳል ያደርጋታል፡፡

ይህ ደግሞ ሀገራትን ከሀገራት ለመለየት ሌላኛው ችግር ሆኖ ሕዝብም አንዱን ሊኖርበት ሲመኝ ሌላው ለጆሮህ ሊሰማው፤ ለዐይን ሊያየው ብሎም ለህሌናው ሊያገናዝበው ይሰቀጥጠዋል፡፡ ለዚህም ነው ሰው ነጋ ጠባ የሰውን ልጅ በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በሀሳቡ እየለካ አብሮት ሊኖር ከሱ ዘንድም ተፈጥሮ ቢሆን ኖሮ ምቾቱ ምንኛ የተሳካ እስኪመስለው በስማኔ የሚመንነው፡፡

በርግጥ አሜሪካ ለዚህ አስገራሚ ምሳሌ ናት፡፡ በማንነት ላይ በሰውነት ክብሩ የሚመጣን ኃይል ፈፅሞ የማትነካ ብሎም በሚነካም የማትደራደር ኃያል መሆኗ ክብር እና ታላቅነትን ልታገኝ ታድላለች በገንዘብ እና በአጉል ትምክት ደግሞ ታላቅ የነበሩት ለሰውነት ክብር ሲነፍጉ የነበሩት ሶርያ፤ ግሪክ፤ የመን ሌሎቹም ላይደረስባቸው ይመስል ያልተነኩ ሀገራት ጭምር የየእጃቸውን እያገኙ ሰውም እንደ ሲኦል እየራቃቸው ይኖራል፡፡

ታድያ ወዳጄ አንተ ሀገር ይኖርህ ዘንድ ትሻ ይሆን ምላሽህ እውነት ከሆነ የጊዜያት እንጂ የሰው ጀግና የለውም እና በተለይ እንደ ኢትዮጲያ ሀገርህ/ሽ አንድ ነገር እናስተውል በየትኛውም የዕርስ በዕርስ ጦርነት ሆነ የሌላ አካል ተለጣፊ ዕልቂት ባመጣኸው ክብር አልባ በሆነ ጦርነት መፍነክነክህን ትተህ፤ አጉል የሆነውን ዘረኝነትህን ቀብረህ ቢነኩህ ብረት አግለው ከፌስታል ሲያስጠጉት ለመኮራመት እሳት ባልነካው ብረት ቢታሹ አጉል ትምክትን በማሶገድ ለተበደለው ይቅርታን እና ሰበዓዊነትን በማላበስ ብሎም የውስጥ ለውስጥ ሥርሰራን በማስወገድ በገዳይህ ለመወደድ ካሻህ ፍቅርን ጥለኸው ከምትሄደውም መሬትህ አቋድሰው ያኔ ምኑም ለማንም ቀለቀል ሆኖ ከሰማይ የራቀህ ሁሉ አጠገብህ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡

የማናውቃት ገነት የምትናፍቀን በአዕምሯችን ስለሳልናት እንጂ ስለኖርንባት ቢሆን ኖሮ ምድርን የሚደርስባት ለሰው ልጅ ሥልጣን የተቸረባት ገነት ባልነበረች ነበር፡፡

እናስ ሀገር ካሻን ምን እናድርግ ይሆን?

በርግጥ ሁሉንም በአንዴ አጥፍቶ ፃድቅ ልሁን ለእብድ የተለኮሰ ቤት ብርሃን ቢመስልም ሀቁ ጥፋት ነው፡፡ ማለትም ሱስን በአንዴ ለመተው ወይም ከዕብደት በቅፅበት ለመዳን ሊከብድ ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ቀን በቀን ክህደት ከሆነው ሀሰተኛ ማንነት በመውጣት፤ ከብልሹ አሰራሮች ራስን በማቀብ ከራስ በፊት ለሌላው የሚለውን ባህል በማዳበር፤ ከወሬ በዘለለ በእውነት እና በተግባር ላይ መገኘት ሲቻል ለሰውነት በተለይ በሰበዓዊነቱ ብሎም ክብር እና ምስጋና መቸር እንዲሁም መጠበቅ ሲቻል ያኔ የምትፈልጋት ሳትሆን ፈልገህ ያጠኃት ሀገር ኖረህ የማትጠግባት ገነት ካንተ ላፍታ ልትሰወርህ አትችልም፡፡

በዋናነት ሀገር የምትሻ ከሆነ ሀገር ማለት ሕዝብ ነው እና ለሕዝብ ክብር እንዲሁም ፍቅር ልትነፍገው አይገባም እና ከክፋት ሰበቃ ብሎም ክፍፍል ራስን በማገልገል ለሌላው አርዕያ በመሆን ሌሎችም ሀገርህን እንዲጠሏት ሳይሆን ሕዝብህም በሄደበት ሀገር አንገቱን ሳይደፋ በኩራት ኖሮ በፍቅር ስሙ እንዲወሳ ማድረግ ሲቻልህ የምትሻት ሀገር ያንተ ትሆናለች፡፡ 

በርግጥ እንደ ቀልድ የለኮስከው እሳት ማቃጠሉን የምታውቀው እሳቱ ሲነድ ነው፡፡ ከዛ ውጪ ግን በአለማችን ላይ ተጠልቶ ተነፍጎ የቀረ ምንም ነገር የለም፡፡ ነገር ግን እየመረረህም ቢሆን እንቆቆ ለድህነትህ ግድ ነው እና የመጣውን ተቀብለን የተሰጠንን አክብረን በጋራ ልንኖር ይገባል፡፡ ሰናይ መልካሙን ሁሉ ለሕዝቤ!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የህዳሴ ግድቡ ውዝግብ በፖለቲካዊ ሳይሆን በቴክኒካዊ መንገድ መፈታት አለበት

በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ፣ እና የመካከለኛው ምስራቅ...

የ7 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ አለመከናወኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሚተዳደሩ 7 የጋራ መኖሪያ...

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ በ80 ዓመታቸው ከዚህ...