የቻይናው ግዙፉ የኤሌትሪክ መኪኖች አምራች ቢ.ዋይ.ዲ በዲዛይንና በባትሪ ተከላ ችግር ምክንያት ከ115,000 በላይ መኪኖችን ለማሻሻያ ወደ ማምረቻ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።
ይህ ችግር የተገኘባቸው ከ2015 እስከ 2017 የተመረቱ ከ44 ሺ በላይ የታንግ እና ከ2021 እስከ 2022 የተመረቱ ከ71ሺ በላይ የዩዋን ፕሮ ሞዴሎች ላይ መሆኑ ተገልጿል።
በዩዋን ፕሮ ሞዴሎች ላይ ያጋጠመው ችግር ባትሪውን ከውኃ እንዲሁም ሌሎች ቆሻሻዎች ለመሸፈን የተገጠመው መከላከያ (Sealing Gasket) በአግባቡ አለመጥበቁ መሆኑ ተገልጿል።
ይህም ውኃ ወይም ሌሎች ነገሮች ወደ ኤሌክትሪካል ሲስተሙ እንዲገቡ እና ተግባሩን ሊረብሹ ይችላሉ።
ተቋሙ በተደጋጋሚ በምርቶቹ ላይ የማሻሻያ ጥሪ ቢያቀርብም ይህኛው ከእስካሁኖቹ በመጠን ከፍ ያለ ነው ተብሏል።
ኩባንያው ፈጠረ ያለውን ችግሮች ከክፍያ ነፃ እንደሚያስተካክል ተናግሯል።
@TikvahethMagazine