በመዲናዋ ሕፃናት እየተጫወቱ የሚማሩባቸው 12 ሺህ የመጫወቻ ስፍራዎች ይገነባሉ

Date:

በመዲናዋ ሕፃናት እየተጫወቱ የሚማሩባቸው 12 ሺህ የመጫዎቻ ስፍራዎች እንደሚገነቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ይህ የተገለፀው 34ኛው የአፍሪካ ህፃናት ቀን በሴቶች አደባባይ በተለያዩ የህፃናት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በተከበረበት ወቅት ነው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመርሃ ግብሩ ላይ በመካፈል ባስተላለፉት መልዕክት፤ የህፃንነት ጊዜ የህይወት መሰረት መሆኑን ገልጸዋል።

ሕፃንነት ላይ መልካም ነገር ከተሰራ የነገዋ ኢትዮጵያ መሪዎችን፣ ትላልቅ የንግድ አንቀሳቃሾችን መገንባት የሚቻልበት ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሕጻናት እየተጫወቱ ቁም ነገር የሚጨብጡበት፣ በአካልና በአዕምሮ የሚጎለብቱበት ስፍራዎችን እየገነባ መሆኑን ገልጸዋል።

ሕፃናት እየተጫወቱ በአካልና በአዕምሮ የሚጎለብቱባቸው ስፍራዎችን ማስፋፋት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በከተማዋ ለህፃናት ሁለንተናዊ ዕድገት የሚበጁ ከ2 ሺህ 130 በላይ የህፃናት መጫወቻ ሥፍራዎች መገንባታቸውን ገልጸው፥ ወደፊት ለመገንባት ከተያዘው እቅድ አኳያ ጅምር መሆኑን ተናግረዋል።

አዲስ አበባን ህፃናት የሚገባቸውን የመጫዎቻ ስፍራ የሚያገኙባት ከተማ እናደርጋታለን ያሉት ከንቲባ አዳነች፥ ወላጆች ልጆቻቸው እየተጫወቱ የሚማሩበትን እድል ሊሰጧቸው እንደሚገባ ገልጸዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በራሱና ማህበረሰቡን በማስተባበር በየትምህርት ቤቶችና በየአካባቢው ህፃናት እየተጫወቱ የሚማሩባቸው ስፍራዎችን መገንባቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢመማ 23ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ እና በአዳማ ከተሞች ተካሔደ

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 23ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻው ሥነ_ሥርዓት...

ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ...