ባለትዳሮቹ በጨርቅ ታስረው ውሃ ወደሞላው ኩሬ ገብተው ሞተው ተገኝተዋል። አሳዛኝ ክስተቱ ነሀሴ 16/2017 ዓ.ም በአክሱም ከተማ ቓላሚኖ የኩሬ ውሃ በሚገኝበት ፅልዐ ተብሎ በሚጠራ ልዩ ቦታ ነው ያጋጠመው።
ጥንዶቹ የክርስትና እምነት ተከታዮች በመሆናቸው ምክንያት በመካከላቸው ለመጋባት የሚከለክል የስጋ ዝምድና ቢኖርም ከመጋባት አልፈው ልጅ እስከመውለድ ደርሰዋል።
የአብራካቸው ክፋይ የ4 ወር ዕድሜ ያለው ጨቅላ ህፃን አፍርተዋል።
የቅርብ የሩቅ ቤተሰብ በመካከላቸው ባለው የስጋ ዝምድና ምክንያት እንዲለያዩ ከምክር ባለፈ የተለያዩ ጫናዎች ያሳድርባቸው እንደነበረ የአከባቢውን ማህበረሰብ ጠቅሶ የትግራይ ፓሊስ ገልጿል።
‘ ተለያዩ ‘ የሚል የዘመድ አዝማድ ጫና የበረታባቸው ጥንዶቹ በአንድ ኩሬ ውስጥ ህይወታቸው አልፎ ተገኝቷል።
ፊት ለፊት ተጣብቀው ራሳቸው በጨርቅ ታስረው ውሃ ወደ ሞላ ኩሬ ገብተው ሞተው ተገኝተዋል ይላል የፓሊስ መረጃ።
” ስለ ጥንዶቹ አሟሟት እስከ አሁን የተገኘው መረጃው በቂና የመጨረሻ አይደለም ” ያለው ፓሊስ ” ስርዓተ ቀብሩ ቢፈፀምም ምርመራው ይቀጥላል ” ብሏል።
@tikvahethiopia