ዘይት ከ20 ሚሊዮን ሊትር በላይ የአቅርቦት ክፍተት አለ

Date:

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዘይት አቅርቦት ከሀገራዊ ፍላጎት አንፃር በእጅጉ ዝቅተኛ መሆኑ ተገልጿል ። የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር እንደጠቆመዉ በአማካይ በየወሩ 56.7 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት እየቀረበ ቢሆንም፣ የሀገሪቱ ወርሃዊ ፍላጎት ግን ከ75 እስከ 80 ሚሊዮን ሊትር ይደርሳል።

ይህ ማለት ከ20 ሚሊዮን ሊትር በላይ የሆነ የአቅርቦት ክፍተት መኖሩን ያመለክታል።

ይህ ከፍተኛ የአቅርቦትና የፍላጎት ልዩነት በገበያ ውስጥ እየታየ ላለው የዘይት ዋጋ ንረት ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

ካፒታል ባደረገው ቅኝት፣ አምስት ሊትር የምግብ ዘይት እንደ መለያው ቢለያይም እስከ 1,650 ብር እየተሸጠ መሆኑን ታዝቧል።

ሚኒስትሩ ትላንት እንዳስታወቀዉ የምግብ ዘይት አቅርቦትን ለማረጋጋት ከታቀደው 121 ሚሊዮን ሊትር ውስጥ፣ እስካሁን 54 በመቶ ያህሉ ማለትም 65 ሚሊዮን 340 ሺህ ሊትር የሱፍ ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ አለመግባቱ ተገልጿል።

ይህ መዘግየት የተፈጠረው ዓለም አቀፍ ጨረታውን ያሸነፉ አቅራቢዎች በመንግስት የልማት ድርጅቶች በኩል በገቡት ውል መሰረት ዘይቱን በወቅቱ ባለማቅረባቸው ነው። መንግስት በቀጣይ ተገቢውን ክትትል እንደሚያደርግ አስታዉቆ ነበር።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የህዳሴ ግድቡ ውዝግብ በፖለቲካዊ ሳይሆን በቴክኒካዊ መንገድ መፈታት አለበት

በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ፣ እና የመካከለኛው ምስራቅ...

የ7 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ አለመከናወኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሚተዳደሩ 7 የጋራ መኖሪያ...

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ በ80 ዓመታቸው ከዚህ...