የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባዔ በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈት የተሰማውን ሐዘን ገልጿል፡፡
ጉባዔው ባስተላለፈው የሐዘን መግለጫ መልዕክት ÷ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በታላቁ አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ትገልጻለች ብሏል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ የብዙዎች አባት፣ የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት ነበሩ፤ ሀገራችን ታላቅ አባትን አጥታለች ሲል ገልጿል፡፡
ከኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር በተለይም በሀገራችን ሰላም እና እርቅን ለማውረድ በርካታ ሥራዎችን በጋራ እንደሰሩም አውስቷል፡፡
ጉባዔው ለቤተቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለእስልምና እምነት ተከታዮች እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡