የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ።
ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ሲደረጉ ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ቼልሲ 8 ሠአት ከ30 ላይ ይገናኛሉ።
11 ሠአት ላይ ሰንደርላንድ ዎልቭስን እንዲሁም በርንሌይ ሊድስ ዩናይትድን ያስተናግዳሉ።
በተመሳሳይ ሠአት ክሪስታል ፓላስ ከ በርንማውዝ፣ ብራይተን ከ ኒውካስትልእንዲሁም ማንቼስተር ሲቲ ከ ኤቨርተን ይጫወታሉ።
ምሽት 1 ሠአት ደግሞ የሊጉ መሪ አርሰናል ከሜዳው ውጭ ከ ፉልሃም ጋር ምሽት1 ከ30 የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል።