ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ለጊዜው አገደ

Date:


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማኅበራት ምዝገባና ቁጥጥር መምሪያ ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ሰጥቶት የነበረውን ፍቃድ ለጊዜው አግዷል።መምሪያው እገዳውን የጣለው ቋሚ ሲኖዶስ በማኅበሩ ሚዲያ የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ነው።
መምሪያው ያስተላለፈው ጊዚያዊ እግድ እንደሚከተለው ይነበባል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ሚያዝያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኀበር ፍኖተ ጽድቅ በተስኘው ሚዲያው በተለያዩ ጊዜያት ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ውጪ ያስተላለፈው ትምህርት የቤተ ክርስቲያኒቱን አባቶች፣ ሊቃውንቱንና መላው ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሳዘነ በመሆኑ ችግሩ ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስ በማኅበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ በኩል  ታግዶ እንዲቆይ በማለት ወስኗል።

ስለሆነም የማኀበራት ምዝገባ፣ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ከቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ለማኀበሩ ሕግን ጠብቆና ተከትሎ ፈቃድ ሲሰጥ ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዶግማ (እምነት)፤ ቀኖናና ትውፊት ጠብቆ እንዲሰራ መሆኑ እየታወቀ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ውጪ በሚዲያው ላስተላለፈው የስህተት ትምህርት ማብራሪያ እንዲሰጥ በተጻፈው ደብዳቤ መሠረት ማብራርያና ምላሽ የሰጠበት ቢሆንም በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ችግሩ ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ድረስ የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኀበር በቤተ ክርስቲያናችን ስም ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርግ የታገደ መሆኑን እየገለጽን የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲደረግ በጥብቅ እናስታውታለን ።በማለት እገዳውን አስተላልፏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

BYD ከ115,000 በላይ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ ማሻሻያ እንደሚያስፈልጋቸው ገለጸ

የቻይናው ግዙፉ የኤሌትሪክ መኪኖች አምራች ቢ.ዋይ.ዲ በዲዛይንና በባትሪ ተከላ...

የትራምፕን ንግግር የህንድ መንግስት ስለ ጉዳዩ ምንም የማዉቀዉ ነገር የለም ብሏል

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሩሲያን ነዳጅ ላለመግዛት መስማማታቸውን...

አቶ አህመድ ሽዴ ከእንግሊዝ የዓለም አቀፉ የልማት እና የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከእንግሊዝ የአለም አቀፍ የልማት...