ስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት የአፍሪካ ሕጻናት ቀንን በድርጅቱ ግቢ ውስጥ አከበረ

Date:

ወላጅ አልባ የሆኑ ሕጻናትን እና ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ ሕጻናት እና ሴቶችን በመደገፍ ላይ የሚገኘው ስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት በዛሬው ዕለት የአፍሪካ ሕጻናት ቀንን በልዩ ሁኔታ በድርጅቱ ግቢ ውስጥ አክብሯል።

በየዓመቱ የሚከበረው የአፍሪካ ሕጻናት ቀን በኢትዮጵያ ለ34ኛ እና በአፋሪካ ለ35ተኛ ጊዜ ነገ ሰኔ 9 ቀን ይከበራል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ አብዱ በመድረኩ እንደገለጹት፤ በዓሉ “የልጅነት ጊዜ ለሁሉም ሕጻናት” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በድርጅቱ ታስቦ ውሏል።

ይህ በየዓመቱ ሰኔ 9 የሚከበረው የአፍሪካ ሕጻናት ቀን  በደቡብ አፍሪካ የሰዌቶ ከተማ ውስጥ የተፈጠረውን የአስከፊ ሀዘን ለማሰብ የሚከበር መሆኑን አስረድተዋል።

“ይህ ቀን መከበሩ ጥራት ያለው ትምህርትና ለሀገር ዘላቂ የሆነ ልማት እንዲኖር የሚያስችል አስተዳደግን የሚፈጥር በመሆኑ የማህበረሰብ ክፍል ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ በዓል” ነው ሲሉም አሳስበዋል።

አክለውም፤ ስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት በአዋጅ ቁጥር1113/2011 በኢፌደሪ ሲቪል ማህበረሰብ  ድርጅቶች ኤጀንሲ በሰርቲፍኬት ቁጥር 0089 በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚሰራ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑን አንስተዋል።

ድርጅቱ ለችግር የተጋለጡ እና የተጎዱ ሕጻናትን ለመደገፍ የተቋቋመ መሆኑን የገለጹም ሲሆን፤ አሁኑ ላይ ከ1 ሺሕ 700 በላይ የሚሆኑ ድጋፍ የሚሹ  ሕጻናት እና እሴቶችን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በተለይም ሕጻናት በቤተሰቦቻቸው ውስጥ እያሉ የምግብ፣ የልብስ፣ የሕክምና፣ የትምህርት ቤት ወጭዎችን የመሸፈን ፕሮግራም ነድፎ እየሰራ እንደሚገኝ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ አብዱ ገልጸዋል።

እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ከቤተሰቦቻቸው የጠፉ ሕጻናትኔ የማገናኘት ሥራዎችን እንደሚሰራ የገለጹ ሲሆን፤ የሕጻናት ቤተሰቦች በዘላቂነት ድህነትን አሸንፈው እራሳቸውን እንዲችሉ የማድረግ ሥራዎችን እንደሚሰራም አክለው አብራርተዋል።

ለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ላለፉት 23 ዓመታት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ እየሰራ እንደሚገኝ በመግለጽ፤ “አሁን ላይ ደግሞ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ላይ ላሉ ወላጆቻቸውን በተለያዩ ምክንያት ላጡ ሕጻናት እና አቅመ ደካማ ቤተሰቦች በመርዳት ላይ ይገኛል” ብለዋል።

“በዚህም የመንግሥት አካል፣ የግል ድርጅቶች እንዲሁም ማህበረሰቡ የኢትዮጵያ ሕጻናት የራሳቸው ቀን እንዲኖራቸው ማድረግ እና በጉድፈቻ ወላጅ ለሚሆኑ  ሰዎች የሕጻናቱን ጥቅም የሚያስከብር መመሪያ በቤተሰብ ሕጉ ላይ እንድካተትልን” ሲሉ ጠይቀዋል።

እንዲሁም “በጉዳዩ ላይ ትኩረት በመስጠት ሕጻናቱን በቤተሰብ ቅርጽ ውስጥ እንዲያድጉ ለማድረግ የታክስ ቅነሳ እንዲደረግ አሳስበዋል

ከዚህ በተጨማሪ ስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት አዲሱን የመለያ አርማውን በመድረኩ አስተዋውቋል።

የመለያ አርማ መለወጥ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት፤ ‘ድርጅቱ የሚያከናውናቸውን ፕሮግራሞች የሚወክል እንዲሆን ከማሰብና ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የአሰራር ሂደትን ለመከተል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው’ ተብሏል።

የአፍሪካ ሕጻናት ቀን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ጋዜጠኞች በተገኙበት ነው የተከበረው።


(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ለሊት እንቅልፍ የለኝም

"አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ያሳስበኛል፤ እኔ አሁን 86 ዓመት...

አዎ ነበሩ ….

🔘የሁሉም አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሓጅ ዑመር🔘ነፍስዎ በሰላም ትረፍ "...

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው የሀይማኖት...