በተደረገ ድንገተኛ የምርመራ ሥራ አለአግባብ የሕጻናት አልሚ ምግብ እርዳታ ሲወስዱ የነበሩ 356 ሰዎች መገኘታቸው ተገለጸ

Date:

የአዲስ አበባ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አደረኩት ባለው ድንገተኛ የምርመራ ሥራ፤ የሕጻናት አልሚ ምግቦችን አለአግባብ በእርዳታ መልክ ሲወስዱ የነበሩ 356 የሚሆኑ ሰዎች መገኘታቸውን ገልጿል።

የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሃድጉ ጸሃዬ፤ በተለያየ መልክ ድጋፍ የሚደረግላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ከወረዳ ጀምሮ በሚደረገው ምልመላ ላይ ችግሮች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ለዚህም በተመረጡ ጥርጣሬ በፈጠሩ አካባቢዎች ላይ በተደረገ የምርመራ ሥራ አለአግባባ የሕጻናት አልሚ ምግብ ሲወስዱ የነበሩ ሰዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ መቻሉ ተናግረዋል።

ይህ “የአመለካከት ችግር ነው” ያሉት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው፤ የተረጂነት ስሜትን ለማጥፋት በርካት ሥራዎችን መስራት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

በማህበረሰቡ ዘንድ “ከእኔ ሌላው ይብሳል” የሚለውን አመለካከት ከመፍጠር አንጻር የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎችን ለመስራት የመገናኛ ብዙሃኑም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተጨማሪም ‘የተስማሚነት ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሆኑ የተመረጡ እገዛ የሚያፈልጋቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሰጡ ለሥራ የሚሆኑ እቃዎች ላይ ከተገቢነት ባሻገር በጠየቁት የሥራ ቁሳቁስ መስራት ይችላሉ’ የሚለውም ጭምር እየተረጋገጠ መሆኑን አክለዋል።

በአጠቃላይ እገዛ ለሚደረግላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ከታች ከወረዳ ጀምሮ የሚደረጉ ምልመላዎች ላይ ሰፊ የሆነ ቁጥጥር በማድረግ ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ሃድጉ ገልጸዋል።

አሐዱ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...