ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው የሀይማኖት አባት ስለሆኑ አይደለም። ‘ሰው’ ሆነው ስለተገኙ እንጂ።
- አላህን እንደሚፈሩ ያያቸው ሁሉ መገንዘብ አያቅተውም።
- ከእውነት ጎን ለመቆም ማንንም አይፈሩም፤ አያስፈቅዱምም።
- ሙስሊም ክርስትያን ሳይሉ ከተበደለ ጎን ይቆማሉ።
- ንግግራቸው ብቻ ያጠግባል፤ ነፍስን ያለመልማል።
- አመራር (leadership) ያውቃሉ። ፕሮሲጀር እንዴት እንደሚጠብቁ አብሯቸው የሰራ ይመስክር።
- ዑለማዎችን (አዋቂዎችን) ያከብራሉ።
- በኢትዮጵያ ጉዳይ ቀልድ አያውቁም። (በአባይ ውሃ አጠቃቀም ዙሪያ በልበ-ሙሉነት ያንፀባረቁት አቋም የግብጽ መሪዎችን እንዴት እንዳነጋገረ እናስታውሳለን)።
- በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰነድ-አልባ የሙስሊሙ መገልገያ ተቋማት (መስጊዶችን ጨምሮ) ይዞታዎች በጥሩ ተግባቦት ህጋዊ መስመር አስይዘዋል።
ሌላም ሌላም ብዙ…. መልካም ነገሮች …
አላህ (ሱ.ወ) የተቀዳሚ ሙፍቲያችንን አፊያ ይመልስልን! 🤲
ሁላችንም በየእምነታችን ዱዓ (ጸሎት) በማድረግ ፈጣሪ ጤናቸውን እንዲመልስላቸው እንለምን! 🤲
ሐዉልት አህመድ