ቻይና አዲስ የሚወለዱ ህጻናትን እንደምታበረታታ ገለጸች

Date:

በቻይና ሆሆት ከተማ አስተዳደር ልጅ ለሚወልዱ እናቶች ለልጁ በየቀኑ አንድ ኩባያ ወተትና ለህጻኑ የእንክብካቤ ድጋፍ እንደሚደረግለት አስታውቀዋል፡፡

በመላው ቻይና በ20 ግዛቶች ይሄንን መሰል ድጋፍ ለሚወልዱ እናቶች እየቀረበ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ፤እነዚህ ድጎማዎች ወጣት ጥንዶች ወደ ጋብቻ እንዲያመሩና ልጆችን እንዲወልዱ ለማበረታታት እንደሆነ የሃገሪቱ ሚዲያ ዢንዋ ዘግቧል፡፡

የቻይና ህዝብ የውልደት መጠን እጅግ ማሽቆልቆሉ መንግስትን ያሳሰበ ጉዳይ ሲሆን፤ አሁን ላይ ያለው የውልደት መጠን ከአንድ ሺ ሰዎች 6.77 በመቶ ብቻ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በዚህም የቻይና መንግስት የስነ ህዝብ ፖሊሲ አውጪዎች ጥንዶች ልጆች እንዲወልዱ አዳዲስ መፍትሄዎች ላይ ጥናቶችን እያደረጉ ነው ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል የ 2023 ጥናት እንደሚያሳየው በቻይና የአዛውንቶች ቁጥር 2መቶ97 ሚሊየን ደርሷል ፡፡

ቻይና 1.4 ቢሊየን የህዝብ ቁጥር ያላት ሲሆን፤ የዓለምን ህዝብ ቁጥር 17.4 በመቶ የሚሆነዉን ትሸፍናለች፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...