በጥራጥሬና ቅባት እህሎች ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ያስገኙ ላኪ ድርጅቶች ዕውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ሽልማቱ በአዲስ አበባ የሳይንስ ሙዚየም «የማይበገር ንግድ እና ዘላቂ የእሴት ሰንሰለቶች» በሚል መሪ ቃል በተካሄደው 15ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ኮንፈረንስ ላይ ተሰጥቷል።
ኮንፈረንሱ በኢትዮጵያ ጥራጥሬና ቅባት እህሎች ላኪዎች ማኅበር ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን፣ ከኅዳር 15 እስከ 16 ቀን 2019 ዓ.ም. ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።
